ምንጮቻችን እንደገለፁት
በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ቃፍታ ሁመራ ወረዳ አዲ ህርዲ ቀበሌ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች ከነዋሪው ህዝብ ሳይረዳዱ የእርሻ መሬት ከአንዱ
በሃይል ነጥቀው ለሌላው በአድልዎ እያደሉ ሲሆኑ በዚህ ምክንያት ደግሞ ህዝብ እርስበራሱ ወደ አልተፈለገ ጥላቻና ድብድብ እየገባ
እንዳለ ታውቋል።
በዚህ ፍትሃዊነት በጎደለው
የእርሻ መሬት መቀማትና ለሌላው ማደል የተነሳ ሃምሌ
30ቀን 2006 ዓ/ም አዲ ህርዲ በተባለው ቀበሌ አበባው ተስፋይ አሸናፊ ከእርሻ መሬቱ ለታደለውን ግደይ ገብረእግብሄር ግደይ ለተባለ
አርሶአደር መሬቴን አታርስም ቤተሰቤን በምን ላስተዳድር ነው በማለት
በጥይት ተኩሶ ከገደለው በኋላ ካካባቢው እንደተሰወረ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።
በመጨረሻም የስርዓቱ ባለስልጣናት ያለአገባብ የአርሶአደሮችን መሬት እየሸነሸኑ
በነዋሪው ህዝብ መካከል ሰላም እንዳይኖር ካላቸው ፍላጎት የተነሳ ምክንያት እየፈጠሩ በማጋጨት በጥላቻ ዓይን እንዲተያዩ እያድረጉ
መሆናቸውን ምንጮቻችን ከስፍራው አስረድተዋል።