Sunday, August 17, 2014

የሽሬ-እንዳስላሴ ከተማ ከንቲባ አቶ መረሳ አታክልቲ ለከተማው ህብረተሰብ ሰብስቦ አንድ ላምስት በሚለው አደረጃጀት ያልተጠረነፈ ሰው የሆነ ይሁን ማህበራዊ አገልግሎት ማግኘት አይችልም እያለ በማስፈራራት ላይ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ከከተማዋ አስታወቁ።



   በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ከሚገኙ የህወሃት ኢህአዴግ ባለስልጣናት መካከል አንዱ የሆነው የሽረ እንዳስላሴ ከተማ ከንቲባ  አቶ መረሳ አታክልቲ የተባለው ካድሬ ስርዓቱ በህዝብ ላይ እየፈፀመው ባለው እኩይ ተግባር ምክንያት ህዝቡ ተማሮ በመጭው 2007 ዓ.ም ለሚካሄደው ምርጫ እንዳይተፋቸው በመፍራት አንድ ላምስት በሚለው አደረጃጀት ውስጥ ያልተካተተ ማነኛውም ዜጋ የዚህ አገር ዜጋ አይደለም እያለ ለከተማዋ ነዋሪ ማህበረሰብ ነሐሴ 4 /2006 ዓ.ም ሰብስቦ ሲያስፈራራቸው  እንደዋለ ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።
  መረጃው አክሎ እንደሚያስረዳው- መሰረታዊ ለምግብ ፍጆታ የሚውሉ እንደ ስኳር፤ዘይት፤የፈርኖ ዱቄትና ተዛማጅ ነገሮች በሽሬ ከተማ ውስጥ እጥረት በማጋጠሙ የከተማዋ ህብረተሰብ ዕለታዊ ኑሮውን ለመምራት እጅግ በጣም ተቸግሮ እንደሚገኝ መረጃው ገልፆ የከተማዋ ነጋዴዎች ቢሆኑም ከልክ በላይ የሆነ ግብር ክፈሉ ስለሚባሉ ምሬታቸውን በማሰማት ላይ ስለሚገኙ ለዚህ ህዝባዊ ስሜት በቁጥጥራቸው ውስጥ ለማስገባትና ለመያዝ እንዲመቻቸው በማለት ህብረትሰቡን ሳይወድ በግድ በማስገደድ አንድ ላምስት በሚለው አደረጃጀት ወስጥ  አቆራኝተው ይዘውት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።