በአዊ ብሄረሰብ ዞን
የሚገኙ ከፍተኛ ባለስልጣናት በብሄራችን ውስጥ ከሌላ ብሄር የመጣ ሊገባብን አይገባም በማለት ዘመድ አዝማዶች አንድ ላይ በመሆን
ስልጣንን በመቆጣጠር ደስ እንዳላቸው የህዝብንና የሃገርን ንብረት እያጠፋፉ መሆናቸውን የተገነዘበ ነዋሪ ህዝብ ተቃውሞውን እየገለፀ
እንደሚገኝ መረጃው አስረድቷል።
በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በዞን አስተዳደር ምክር ቤት 3 ጥንድ ባልና
ሚስቶች የሃላፊነት ቦታን በመያዝ የግላቸውን ሃብት መሰብሰብ እንጂ ለህዝቡ ምንም ዓይነት አገልግሎት እንደማይሰጡና በተጨማሪም እኒህ
ባለስልጣኖች በአንከሻና ጓጉሳ ወረዳዎች ዘመዶቻቸውን አስቀምጠው እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል።
እኒህ በዘመድ አዝማድ ስልጣን የተቆጣጠሩ የዞን አስተዳዳሪዎች ቡድን ከ2.5
ሚሊዮን ብር በላይ የህዝብ ሃብት ዘርፈው በመውሰድ ከ1200 ሄክታር በላይ የእርሻ መሬት በኢንቨስተር ስም ለራሳቸውና ዘመዶቻቸው
እየተጠቀሙበት እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።