Friday, August 22, 2014

ባገር ደረጃ የተደረገውን የሰራተኞች ደሞዝ ጭማሪ ከፍተኛ ደሞዝ ለሚወስዱት ክፍል ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ ከፍተኛ ተቓውሞ እያስነሳ መሆኑን ምንጮቻችን ገለጹ።



ስልጣን ላይ የሚገኘውን የወያኔ ኢህአዴግ መንግስት ካለፈው ሃምሌ ጀምሮ መንግስት ለሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ አድርጌያለሁ በማለት በመገናኛ ብዙሃን ይፋ ያደረገውን ከ 1,244 ብር በላይ ደሞዝ ለሚወስዱ ካድሬዎችና አባላቱ ለመጥቅም ሲል ያደረገው በመሆኑ ዝቅተኛ ደሞዝ የሚከፈላቸው ሰራተኞች ተጠቃዊዎች ካለመሆናቸው በላይ በተደረገው ጭማሪ ምክንያትና እሱን ተከተሎ በተከሰተው የኑሮ ውድነት ለከፋ ችግር ተጋለጥን በማለት በስርአቱ ላይ ከባድ ተቃውሞ በማካሄድ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
    ባሁኑ ግዜ ከ1,244 ብር በላይ ደሞዝ ለሚከፈላቸው የመንግስት ሰራተኞች ለሆዳቸው የሚያድሩ የስርአቱ ተላላኪዎች እንደሆኑና ከ1,244 ብር በታች የሚወስደውን ሰራተኛ በተደረገው ጭማሪ ኑሮው እንዳልተሻሻለና በዋጋ መናር ምክንያት ወደ ከፋ ችግር በመግባታቸው ምክንያት በያሉበት አካባቢ ተደራጅተው ለተደረገው የደሞዝ ጭማሪ አጥብቀው እየተቃወሙት መሆናቸውን ጨምሮ አስታውቋል።
 ተቃውሞ እያሰሙ ከሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የራስ ደስታ ትምህርት-ቤት መማህራን፤ በጎንደር ላይ ጋይንት ወረዳ ውስጥ በሚገኘው ከፍተኛ ትምህርት-ቤት መማህራንና በአዊ ዞን አንከሻ ወረዳ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችና ሌሎች መሆናቸውን ይህም ተቃውሞ በመላው የአገራችን ክፍል ተባብሶ እንደሚገኝ ለማውወቅ ተችሏል።