Tuesday, August 5, 2014

በአማራ ክልል በሚገኙ ከተሞች በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተቀጥረው የሚሰሩ በርካታ ዜጎች አሸባሪ የሚል ጥላሸት እየተቀቡ አድራሻው ወደ አልታወቀ እስር ቤት ተወስደው እየተሰቃዩ መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ።



በብዓዴን ኢህአዴግ  ካድሬዎች አሸባሪና ፀረ ልማት በሚል እየተጠረጠሩ ሰላማዊ ዜጎች ወደ አልታወቀ ስፍራ እየተወሰዱ መታሰራቸውን የገለፀው መረጃው ለቀጣይ 2007 ምርጫ ህዝብን ሊያነሳሱ ይችላሉ ያሏዋቸውን ዜጎች ከግንቦት 7 ዋና ፀሃፊ ከአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በተገኘ መረጃ መሰረት ግንኙነት አላችሁ በማለት ከደብረ ማርቆስ ከተማ 4 የመንግስት ሰራተኞች፤ ከባህርዳር ከ8 በላይ ነጋዴና የመንግስት ሰራተኞች። ከጎንደር 6 ምሁራኖች መታሰራቸውን ተገልጸዋል።
   በክልሉ ውስጥ ለጊዜው ያልታወቁ ዜጎች በጨለማና በስውር አድራሻው ወደ አልታወቀ ስፍራ እየተወሰዱ እየተሰቃዩ መሆናቸውን የደርሰን መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።