Tuesday, August 5, 2014

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ የሚኖሩ የሌላ ብሄር ተወላጆች ከአቅም በላይ የሆነ ግብር እንዲከፍሉ እየተገደዱና ድርጅታቸውም እየተዘጋ መሆኑን ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ።



በክልሉ የሚገኙ የሌላ ክልል ተወላጅ የሆኑ ዜጎችን ገዥው የኢህአዴግ መንግስት ከስራቸው ጋር የማይመጣጠን ግብር እንዲከፍሉ በማስገደድ የመክፈል አቅም የሌላቸውን ደግሞ እያሰረና እያሰቃየ እንደሚገኝና ድርጅታቸውንም እየተዘጋ መሆኑን ተገለፀ።
   ሰበብ ተፈጥሮ ድርጅታቸው ከተዘጋባቸው ዜጎች መካከልም ወጣት ሃብታሙ ወርቄ የተባለው የአማራ ብሄር ተወላጅ ሰራተኞችን ቀጥሮ ለአመታት ሲሰራበት የቆየውን የወንዶች የውበት ሳሎን ድርጅት የስራ ፈቃድህ አልታደሰም በሚል ምክንያት ፈቃዱን ቀምተው ከወሰዱበት በኋላ ከፍተኛ ግብር እንዲከፍል ቢያስገድዱትም እንደማይከፍልና ያን ያህል ለመክፈል አቅም እንደሌለው ስለገለፀላቸው ብቻ ድርጅቱን እንደዘጉበት የገዥው መንግስት ግፍና ሰቆቃ ዋቢ በማድረግ የደረሰን መረጃው  አክሎ አስረድተዋል።