Sunday, August 17, 2014

በትግራይ ምእራባዊ ዞን ሉግዲ አካባቢ የሚገኙ የፌደራል ፖሊስ አባላት ሰዎችን እየላኩ የሱዳናዊያን በጎችን እየዘረፉ እንዳሉ ምንጮቻችን ካከባቢው ገለፁ።



በመረጃው መሰረት በትግራይ ምእራባዊ ዞን በሉግዲ አካባቢ የሚገኙ ፌደራል ፖሊስ ተላላኪዎቻቸው ወደ ጎሮቤት ሃገር ሱዳን በመሄድ ከ80 በላይ በጎች ሰርቀው እንዳስረከቧቸው መረጃው በመግለፅ የበጎቹ ባለቤቶች የሆኑት ሱዳናዊያን ተከታትለው በጎች ወዳሉበት የፌደራል ፖሊስ ፅህፈት ቤት በመሄድ በጎቻቸው እንዲመሊሱላቸው ጥያቄ ባቀረበበት ግዜ ምንም ወንጀል ሳይሰሩ ተመልሰው ሱዳናዊያኑ እንዳሰሯቸው ለማወቅ ተችሏል።
     ጥያቄ በማቅረባቸው ብቻ በፌደራል ፖሊስ እንዲታሰሩ ከተደረጉ በኋላ በጎችን ከፌደራል ፖሊስ ፅህፈት ቤት አከባቢ አውጥተው አድራሻው ወደ አልታወቀ ቦታ ወስድው በመደበቅ ሱዳናዊያን  ባለበጎች ደግሞ አስረው ወደቦታቸው እንደመለሷቸው የደረሰን መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።