Sunday, August 17, 2014

በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ የፖሊስ እጅ ያለበት ስርቆት በሰፊው እየተካሄደ በመሆኑ። ነዋሪዎች በስርዓቱ ላይ ምሬታቸውን እየገለፁ መሆናቸውን ምንጮቻችን ከከተማዋ ገለፁ።



   በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ሽሬ እንዳስላሴ ከተማ የሚገኙ ፖሊሶች በስርቆት ስራ ላይ የተሰማሩ ሲሆን በዚህም የተነሳ  በኮሚኒት ፖሊስ አጠገብ  የሚገኝ የአቶ ማህመድ ዑስማን የጨርቃ ጨርቅ ሱቅ ነሐሴ 1/2006 ዓ.ም መዝጊያውን ሰብረው በመግባት በውስጡ የነበረውን ከ20 ሺ ብር (ሃያ ሺ ብር)  በላይ የሚገመት ንብረት እንደሰረቁት ሊታወቅ ተችሏል።
    ስለተፈፀመው ስርቆት የሱቁ ባለቤት አቶ ማህመድ ዑስማን ለሚመለከታቸው አካላት ቀርቦ ሲናገሩ የሰረቃችሑት ፖሊሶቹ ናችሁ፤ ሌላ ሰው ከፖሊስ ፅሕፈት ቤት ድረስ መጥቶ ሊሰርቀኝ አይችልም መዝጊያውን ሰብሮ ቢሰርቅም እዚያው ደጃፍ ላይ የሚያድሩት ፖሊሶች ይሰሙት ነበር። ስለዚህ ንብረቴን የሰረቃችሁት እናንተ ወይም በአባሎቻችሁ ትብብር ነው ሊፈጸም የሚችል በማለት በፖሊሶች ላይ ያላቸውን  ጥርጣሬ እንደገለፁ መረጃው አስታውቋል።
የተሰረቀው ንብረት ለማጣራት የሞከሩ የፖሊስ አዣዦች ቢሆኑም ስርቆቱ የፖሊስ እጅ እንዳለው ካወቁ በኋላ ጉዳይ በህዝብ ፊት እንዳይጋለጥ በመስጋት የማጣራት ስራ ከነአካቴው መተዋቸውን የተገነዘበ የከተማዋ ነዋሪ ህዝብ ፖሊስ የዚሁ ዓይነት ወንጀል ፈፅሞ አገብስብሰህ የሚታለፍ ከሆነ ታዲያ ማንነው ሕግ የሚያከብረው በማለት ጥያቄዎች እያሰማ እንደለ ለማወቅ ተችኋል።