በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን ማንቡክና ግልገል በለስ ወረዳ ነዋሪዎች
ለአመታት ሲጠቀሙበት የቆዩትን የእርሻ መሬት በአስተዳዳሪዎች ትዕዛዝ እየተቀማ ለኢንቨስተሮች እንደተሸጠ መሆኑን የገለፀው መረጃው
በዚህ ምክንያት ደግሞ አሰራሩ ህጋዊ አይደለም በማለት የተቆጡ አርሶ አደሮች እንደማስጠንቀቂያ በኢንቨስተሮች የተዘራውን ሰብል ከብቶቻቸውን
በማስገባት እያበሉትና እያበላሹት መሆናቸውን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።
ከክልሉ ሳንወጣ በአሶሳ ከተማ መንግስት ያሰማራቸው ፀረ ሽምቅ ጉጅሌ በሚል
የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ሃይሎች በሴቶች ላይ አስገድዶ መድፈር እየፈፀሙ
በመሆናቸው እኒህ ወገኖችም ለኤች አይ ቪ በመጋለጣቸው ለስነ አዕምሮ ጫናና ለተላላፊ በሽታዎች እየተዳረጉ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል።
የስርዓቱ ታጣቂዎች
ምንም ወንጀል ያልፈፀሙ የአካባቢው ነዋሪዎችን አስረው እየቀጠቀጡ
እያሳቀዩአቸው መሆናቸውን መረጃው ገልፆ ይህ ግፍፍ ከተፈጸመባቸው ወገኖች አንዱ አቶ ያየህ የተባለው ሲሆን በደርሰበት ከባድ ግርፋትና ድብደባ
አካሉ እንደጎደለና ሚስቱም በሁለት ታጣቂዎች እንደተደፈረች ለማወቅ ተችሏል።