Saturday, August 30, 2014

ሰማእቶቻችን ለዘለአለም እየታወሱ ይኖራሉ!



    የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል መነሻው ጭቁኑ ህዝብ ለበርካታ አመታት ያህል በላዩ ላይ ይካሄድ የነበረውን ቤሄራዊና መደባዊ ፀረ ህዝብ ያገዛዝ ቀንበር መሆኑ በግልፅ ይታወቃል፣ በዚህ መሰረትም በላዩ ላይ ይደርስበት የነበረውን ከልክ ያለፈው ግፍና በደል ለማስወገድ ሲል ክቡር መስዋእትነት ከፍሏል።
     ይህ ከረጅም አመታት በፊት የተጀመረውንና ከተለያዩ ማህበራዊ ኑሮውን ተፈናቅሎ ትግል የጀመረውን ያገሪቱ ወጣት ሃይል። ክቡር  ህይወቱን ከፍሎ ሁል ግዜ በታሪክ መዝገብ አንዲወሳ፤ ያለውን አቅምና ብቃት ተጠቅሞ ከሱ የሚጠበቀውን ግዴታ እንዲያበረክት፤ በገባበት የትግል አላማ ተሰልፎ አኩሪ ገድል ፈፅሞ በክብር እንዲያልፍና በደሙ ወርቃዊ ታሪክ አጽፎ የህዝቡን ጥቅም ለማስከበር በማለት ብቻ ነው።
    ቢሆንም በትግሉ ወቅት ተስልፎ መተኪያ የሌለውን ሂወት ከፍሎ ታሪካዊ ግዴታውን ፈፅሞ ወደ ድል ከደረሰ በኃላ ግን በሂወት ወደ መጨረሻው የድል አፋፍ እደርሳለሁ የሚል አስተሳሰብ ባይኖረውም ያአጋጣሚ ጉዳይ ሆኖ ከመስዋእት ለተረፉ ጀግኖች አስፈላጊውን ክብር፤ ታሪክ ሰርቶው መስዋእት ለከፈሉም የሚገባቸውን ዝክር ከማድረግ ፈንታ። አሳዛኝና አስገራሚ በሆነ መንገድ እንዲባረሩና ደማቸውም ደመ ከልብ ሆኖ እንዲቀር ተፈርዶባቸዋል።       
    እንዲፃፍና እንዲነበብ ተፈልጎ ያለውን ቁምነገር ግን ይህ በተደጋጋሚና በየግዜው ሲነገርለት የቆየውን ጉዳይ ለመድገም ሳይሆን ባለፈው ሳምንት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ሁለተኛውን ዓመት አስመልክቶ በተካሄደው ዝክር። አንድ ነገር ለማለት ፈልገን ነው። 
     አገራችን ኢትዮጵያ ብዛት ያላቸውና የተሟላ አቅም የነበራቸው አገርን ሊመሩ የሚችሉ ታጋዮች በመስዋእትነት ምክንያት ያጣች፤ በየግዜው ወደ ስልጣን በሚወጡ ጸረ ህዝብ ገዢዎች ምክንያት አገራቸውን ትተው በተለያዩ አገሮች የተሰደዱ ሊቃውንቶች፤ ከዛም ባሻገር አገር ውስጥም ቢሆን አስከፊውን ግዜ እስኪያልፍ ድረስ በትእግስት የሚጠባበቁ ብቃት ያላቸውን ዜጎች መኖራቸው ቢታወቅም የወያኔ ኢህአዴግ አመራሮች ግን ለሁሉም ታጋዮች በሚዘክር መንገድ ታሪክን መዘገብ ሲገባቸው ያብዛኞቹ ጀግኖች ታሪክ በመክዳት የአንድን ግለሰብ ስራና በትግሉ ግዜ የነበረውን ግለሰባዊ ሚና እያነሱ ማርገብገባቸው እጅግ የሚያሳዝን ተግባር ነው።
    በአሁኑ ግዜ ባገራችን ላይ በወያኔ ኢህአዴግ ስር ሆነው እየተሰሩ ያሉ እንዳንድ የህዝቡን ጥቅም የማያረጋግጡ ግንባታዎች በህዝቡ መስዋእትነት የመጣ ለውጥ ነው የሚል አስተሳሰብ እንዲኖር ከማድረግ ፈንታ በአንድ ግለ ሰብ የተከሰተ ልዩ ተአምር እንደሆነ ተደርጎ መቅረቡ ታሪክን ሰርተው ላለፉትና የለውጥ ሃዋርያ ለነበሩ ጀግኖች ታሪካቸውን ማራከስ ከመሆን አልፎ ሌላ ትርጉም ሊያሰጠው አይችልም።
   የወያኔ ኢህአዴግ ባለ ስልጣኖች ባገሪቱ ወስጥ ሰራናቸው የሚሏዋቸውን አንዳንድ ግንባታዎችና ሌሎች እንቅስቃሴዎች መለስ ዜናዊ በጠነሰሰው ፖሊስዎችና ስትራተጂዎች የመጡ ናቸው ብለው መግለጻቸው በኢህአዴግ ውስጥ ከመለስ በስተቀር  ሌላ አእምሮና ብቃት ያለው አመራር እንዳልነበረና አሁንም እንደሌለ የሚያሳይ መሆኑንና ከመለስ ዜናዊ ሞት በኃላ የምንለውጠው ፖለቲካዊ መስመር የለም ብለው መሪያቸው በጠነሰሰውና ትቶላቸው በሄደው ፀረ ህዝብ አቅጣጫ እንዲጓዙ መምረጣቸው ደግሞ ከተቀመጠው እቅጣጫ በላይ ስንዝር ያህል የመሄድ ብቃትና አቅም እንደሌላቸውና ፍፁማዊ በሆነ ሞግዚታዊ አስተሳሰብ ላይ መዘፈቃቸውን የሚያሳይ ነው።