Monday, September 22, 2014

የዳንሻ ከተማና ያካባቢው አስተዳዳሪዎች በፅህፈት ቤታቸው ቀርበው ፍቃድ ሳይጠይቁ ወደ እርሻ መሬታቸው ለተሰማሩ አርሶ አደሮች ሽፍቶች ናችሁ በማለት እያሰርዋቸው እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



በትግራይ ምዕራባዊ ዞን፤ ፀገዴ ወረዳ፤ ዳንሻና አካባቢው ውስጥ የሚገኙ በእርሻ ስራ ላይ የሚተዳደሩ እርሶ አደሮች የዘሩትን እህል ሄደው ለመከታተል ሲፈልጉ ከስርአቱ አስተዳዳሪዎች ፍቃድ ውጭ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ መነገራቸውን የገለጸው መረጃው ይህንንም ሳያደርጉ ለተንቀሳቀሱ ሰዎች ሽፍቶችና የሽፍታ ተባባሪዎች የሚል ስም እየተለጠፈባቸውና እየታሰሩ መሆናቸውን ምንጮቻችን ከአካባቢው በላኩት  መረጃ ለማወቅ ተችሏል።
   ህጋዊና ሰላማዊ ሰዎች ሆነው እያሉ ሽፍቶች ተብለው ከታሰሩት አርሶ አደሮች ውስጥ ለመጥቀስ ያህል አስፋወሰን ክንፈ፤ ይርጋ አላምረውና ሌሎች ስማቸው ያልተጠቀሱ ንፁሃን ዜጎች ሲሆኑ ነሃሴ 28/2006 ዓ/ም ከእርሻ መሬታቸው ወደ መኖርያ ቤታቸው ሲመለሱ ሽፍቶች ናችሁ በማለት ተይዘው መወሰዳቸውና እስካሁን የት እንደገቡ እንደማይታወቅ መረጃው አክሎ እስረድቷል።