Tuesday, September 2, 2014

ሽሬ እንዳስላሴ ከተማ በሚገኘው ፖሊስ ጣብያ ውስጥ ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት ሲሰቃዩ የቆዩት ሦስት ሰዎች ነሃሴ 6/2006 ዓ/ም ክእስር ቤቱ እንዳመለጡ ተገለፀ።



ታማኝ ምንጮች ከከተማው የላኩልን መረጃ እንዳመለከተው በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ የሚገኘው ፖሊስ ጣብያ ይለምንም ምክንያት ሲሰቃዩ የቆዩት 3 ሰዎች በሌሊት በሩን ሰብረው ከእስር ቤቱ ማምለጣቸው ለማወቅ ተችሏል።
    ታሳሪዎቹ በማምለጣቸው የተናደዱት የፖሊስ ጣብያው የበላይ አዛዦች ሆን ብላችሁ ነው እንዲያመልጡ ያደረጋችሁት በሚል ምክንያት ከፖሊስ አባላቶቻቸው አራት ሰዎች ማሰራቸውን የገለፀው መረጃው የታሰሩትን የፖሊስ አባላት ስም ዝርዝርም።
-    ምክትል ኮማንደር ይርጋ ግደይ
-    ኢንስፔክተር ምሩፅ
-    ኮንስታብል ጎደፋና ለግዜው አንድ ስሙ ያልታወቀው ግለስብ እንደሆኑ መረጃው አክሎ አስረድተዋል።