Monday, September 22, 2014

የሽሬ እንዳስላሴ መብራት ሃይል ሃላፊዎች ለተገልጋዮች በማጭበርበር የማይገባቸውን ሃብት በማካበት ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ ምንጮቻችን ገለጹ።



      በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ሽሬ እዳስላሴ ከተማ የመብራት ሃይል ሃላፊ አቶ መኮነን የተባለው ባለ-ስልጣን ስልጣኑን ተገን በማድረግ ቆጣሪ ያጣውን የከተማዋን ህዝብ ቆጣሪ ሰለመጣልን ቅድሚያ እንድታገኙ አደርጋችሁአለሁ በማለት የማይገባውን ገንዘብ እየተቀበለ ለግል ጥቅሙ እያዋለው እንደሆነ ተገለጸ።
      መረጃው ጨምሮም የሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ህዝብ እያጋጠመው ባለው የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ምክንያት እየተሰቃየ መሆኑን በመግለጽ አገልግሎት እንዲያገኝ የፈለገ ሰው ወደ ከተማዋ መብራት ሃይል ጽህፈት ቤት በሚሄድበት ሰዓት ሰራውን በግዜው ለማከናወን ከፈለገ የግድ ከታችኞች ሰራተኞች እስከ የበላይ ሃላፊዎች ጉቦ መክፈል እንደሚገባው በመግለጽ በተለይ ድግሞ የጽሕፈት ቤቱ ሃላፊ የሆነው አቶ መኮነን የማይተገበር ቃል በምግባት ገንዘብ ክፈሉኝ እያለ ከበርክታ ሰዎች ከልክ በላይ ገንዘብ እየተቀበለ መሆኑንና     የሃላፊው አካሄድም በህዝቡ ስለተነቃበትና በላዩ ላይ ብዙ አቤቱታዎች ስለ ቀረበ ለማስመሰል ሲባል ብቻ ስርዓቱ በቁጥጥር ስር ላይ  እንዳዋለው ለማወቅ ተችሏል።