Tuesday, September 2, 2014

በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ሽራሮ ከተማ የሚገኘው የመጓጓዣና ትራንስፖርት ክፍል ለተጓዦች ከመጠን በላይ ክፍያ እየጠየቃቸው በመሆኑ ምክንያት ተገልጋዮቹ ምሬታቸውን እያሰሙ እንደሚገኙ ምንጮቻችን አስታውቁ።



   ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሸራሮ ወደ ሁመራ ለሚጓዝ ሰው ለነፍስ ወከፍ ከ170 ብር በላይ እንዲከፍል የሚገደድ ሲሆን በዚህ ህጉን ያልተከተለ የክፍያ ስርዓትም ዋነኛው ተጎጂ ሁኖ ያለው ወደ ስራ የሚመላለሰው ድኻው የህብረተሰብ ክፍል እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
   በዚህ ከአቅም በላይ በሆነ ክፍያ የተማረረው የህብረትሰብ ክፍል መፍትሄ ለማግኘት ሲል ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄውን ያቀረበ ቢሆንም ለዚህ ጉዳይ ሰምቶ ምላሽ የሚሰጥ አካል እስካሁን ማግኘት እንዳልተቻለ ለዚህ ችግር ተጋላጭ የሆኑትን ዜጎች መስረት በማድረግ ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።