እነዚህ በነቀምትና ወለጋ ከተማ የሚገኙ በውትድርና የነበሩ ወገኖች እያጋጠማቸው
ያለውን የኑሮ ችግር ለማቃለል በማለት በማህበር ተደራጅተው መስራት የሚችሉበትን ቦታ ይሰጠን ብለው ላቀረቡት ጥያቄ በአስተዳደሩ
ተገቢውን ምላሽ እንዳላገኙ የገለጸው መረጃው በዚህ ምክንያትም ወደ
ስደት እያመሩ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው ጨምሮም
የከተማው አስተዳዳሪዎች ወታደሮቹ ተደራጅተው መስራት ከጀመሩ በመንግስት ላይ አደጋ ሊፈጥሩ ይችላሉ በማለት ማህበሩ እንዲፈርስ ከፍተኛ ጥረት ያደርጉ እንደነበር የገለጸው መረጃው ስራ የፈቱ ወታደሮችም ባልተፈለገ ስፍራዎችና ለመጠጥ ስሶች ተጠቂ ሆነው እንደሚገኙ መረጃው
ጨምሮ አስረድቷል።