Monday, October 27, 2014

በትግራይ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ከጥቅምት 2 እስከ 6 2007 ዓ/ም ጀምሮ ለካድሬዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ከፍተኛ ተቃውሞ እንደተነሳ ምንጮቻችን ገለፁ፣




ምንጮቻችን ከመቐለ ከተማ እንደገለፁት። በክልል ደረጃ በአቶ አባይ ወልዱ እየተመራ የሰነበተው የካድሬዎች ስብሰባ። በተሰብሳቢዎች ሃይለኛ ጥያቄና ተቃውሞ እንዳጋጠመው ከገለፀ በኋላ። ዋናው የመሰብሰቢያ አጀንዳም የትግራይ ህዝብ ለምንድነው ለህወሓት እየተቃወመ ያለው?፤ የቀድሞ ታጋዮች አካል ጉዳተኞች ማህበር ጭምር ከተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ተሰልፈው እየተቃወሙን ናቸው፤ የዚህ ዋነኛ ምክንያት ምንድነው? የሚሉና ሌሎች አጀንዳዎችን የያዘ እንደነበረ ታውቋል፣
    በተሰብሳቢዎች የቀረቡት ጥያቄዎችን ለመጥቀስ። ህዝቡ በማህበራዊ ችግር እየተሰቃየ ስለሆነ ይህ ችግር ሳይፈታ ሊደግፈን አይችልም፤ ከታች እስከ ላይ ባሉት የመንግስት ፅህፈት ቤቶች መልካም አስተዳደር የሚባል ነገር የላቸውም፤ የትግራይ ህዝብ ተጠቃሚ አይደለም፤ በተለይ ደግሞ የቀድሞ ታጋዮች የተገባላቸው ቃል ስላልተተገበረላቸውና በሌሎችም  ችግሮች ምክንያት ህወሓት ኢህአዴግን ሊቃወሙ እየተገደዱ ያሉበት በማለት እንደተናገሩ ለማወቅ ተችሏል፣
     የመድረኩ መሪ አቶ አባይ ወልዱ በበኩሉ። ከመድረኩ ለተነሱ ጥያቄዎችና ተቃውሞዎች ለመመለስ ከአቅሙ በላይ ስለሆነበት። የፌደራል ባለስልጣናት አቶ ደብረፅዮን ገብረሚካኤልና አቶ አባይ ፀሓየ ከአዲስ አበባ ተጥርተው በመምጣት ስብሰባውን ሊያግዙት  እንደተገደዱ መረጃው ጨምሮ አስረደቷል፣