Monday, October 27, 2014

በኢህአዴግ መከላከያ ሰራዊት በቅርብ ቀን የተሰጠው የጀኔራሎች ማዕረግ በሰራዊት ከፍተኛ ተቃውሞ እያጋጠመው እንዳለ ታወቀ፣




በምንጮቻችን መረጃ መሰረት። በቅርብ ቀን ለጀነራሎቹ የተሰጠው የማዕረግ እድገት። በሰራዊቱ ያለውን ጠብና መቃቃር ሳይፈታ  የተሰጠው ሹመት።  ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው በማለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት እየተነጋገሩበትና በአንዳንድ የሰራዊት አባላት ከፍተኛ የተቃውሞ ስሜት እንደተፈጠረ ለማወቅ ተችሏል፣
   በመከላከያ ሰራዊት ሲካሄድ የሰነበተውና አሁንም እየቀጠለ ያለው ስብሰባ። ከመከላከያ ሰራዊት ለአመታት አገልግለው በቅርብ ወራት ካለምንም  መቋቋሚያ የተሰናበቱት የመከላከያ ሰራዊት አባላት መሰረታዊ ስህተት ተፈፅሟል በማለት አዳዲስ ሃሳቦች እያነሱ እንዳሉ ለመረዳት ተችሏል፣
   ይህ በእዲህ እንዳለ። አሁን እየተካሄደ ያለው የስብሰባ አጀንዳም በመጪው ግንቦት 2007 ዓ/ም በሚካሄደው ምርጫ ላይ ለሚነሳው ተቃውሞ ሊያግዙ አይችሉም ያሏቸውን ወታደሮች ለማባረር ያለመ መሆኑን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣