Monday, October 27, 2014

የበራሕለ ወረዳ ህዝብ የባንዴራ ቀን እንዲያከብር በገዥው ስርአት ካድሬዎች የተሰጣቸውን ትእዛዝ በመቃወም። በአሉ ወደ ሚከበርበት ቦታ እንዳልሄዱ ተገለፀ፣




ታማኝ ምንጮቻችን በላክሉን መረጃ መሰረት። በአፋር ክልል በራሕለ ወረዳ የሚገኝ ህዝብ። የባንዴራ ቀን እንዲያከብር ተብሎ በስርአቱ ካድሬዎች ትእዛዝ ቢሰጠውም። መንግስት የባንዴራ ቀን አክብሩ ከማለቱ በፊት። ህዝቡ ውስጥ ያለውንና እልባት ያለተገኙለትን ችግሮች መፍትሄ ማበጀት በተገባው ነበር በማለት ተቃውማቸውን እንደገለፁ ለማወቅ ተችሏል፣
     በአፋርና በትግራይ ክልል ያለውን የመሬት አስተዳደር መነሻ ያደረገ ከፍተኛ ግጭት መፍትሄ ሳይደረግበትና  ቅንነት ያለው የአስተዳደር ሁኔታ ሳይረጋገጥ። የባንዴራ ቀን ተብሎ በዓል መከበሩ ፋይዳ የለውም በማለት እንደተቃወሙትና። የበታች ሃላፊዎችም ቢሆኑ ከህዝቡ ጋር በማበር ለተነሳው ተቃውሞ እንደደገፉት መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣