Wednesday, October 29, 2014

በአላቂ እቃዎች እጥረት እየተሰቃየ ያለውን ህዝብ በሚመጣው 2007 ዓ/ም ምርጫ ላይ ሌሎችን ድርጅቶች እንዳይመርጥ በሚል ምክንያት በገዢው ኢህአደግ መንግስት ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ከፍተኛ የስኳር አቅርቦት እንደሚቀርብ ተገለፀ፣





ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ እንደሚያመለክተው በአሁኑ ግዜ በሃገራችን አጋጥሞ ባለው የአላቂ እቃዎች አቅርቦት እጥረት ምክንያት፣ የህዝቡ ምሬት ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዳይሽጋገርና፤ ህዝቡ ለተቃዋሚ ድርጅቶች እንዳይመርጥ የሰጉት የኢህአዴግ  ባለስልጣኖች፤ ለነፍስ ወከፍ  ክልሎች 10ሺ ኩንታል ስዃር እየላኩ እንዳሉ በሚድያዎቹ የተገለፀው መረጃው፤ ከሃቅ የራቀ አሉቧልታ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፣
  መረጃው በማከልም በተለይ በትግራይ ክልል አጋጥሞ ባለው የዘይት፤ ስኳርና ሌሎች አላቂ እቃዎች የፈጠረው ማህበራዊ ችግር ሊፈታ ነው ብለው በሚድያ ቢቀሰቅሱም እንኳ፤ እየላክነው ነው ያሉት አቅርቦት  ከህዝቡ ጥያቄ ጋር ሲነፃፀር ፍፁም እንደማይገናኝና ለይስሙላ ተብሎ በመንግስት የቀረበው መፍትሄም ለምርጫ ተብሎ የተሴረ ተንኮል መሆኑና ህዝቡም በንቃት አየተከታተለው እንደሆነ   መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣