Wednesday, October 29, 2014

የሸራሮ ከተማ ፖሊሶች ምንም አይነት ወንጀል ባልፈጸሙት ከ 28 በላይ ወገኖችን አስረው እያሰቃይዋቸው እንደሆኑ ተገለጸ፣





በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ሸራሮ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የወያኔ ኢህአዴግ ፖሊስ አዛዦች ከህግ ውጭ በሆነ መንገድ ሰዎችን አስረው እያሰቃዩ መሆናቸውን የገለጸው መረጃው፤ በአሁኑ ግዜ ፀረ ህዝብ ተግባራቸውን በመቀጠል ከ 28 በላይ ንፁሃን ወገኖችን ለረጅም ግዜ በማሰር እያሰቃዩዋቸው እንደሆኑ፤ ምንጮቻችን ከላኩት መረጃ ለማወቅ ተችሏል፣
    በሸራሮ ከተማ ፖሊስ ጣብያ ውስጥ በድብቅ ታስረው እየተሰቃዩ ከሚገኙ ዜጎቻችን የተወሰኑትን ለመጥቀስ።- በሃቦሎምዓዲ ፀፀር በሚል መጠርያ የሚታወቅ፤ ብአምላኬ የተባለ የአማራ ብሄር ተወላጅና ሌሎችም እንደሚገኙባቸው ተገልጿል፣
    በተመሳሳይ በታህታይ አድያቦ ወረዳ፤ ዓዲ አሰርና ዓዲ ፀፀር ቀበሌዎች የሚኖሩ ከ20 በላይ ነዋሪዎች፤ ያልተስጣችሁን መሬት አርሳችኋል ተብለው መከሰሳቸውና፤ ክሱን የተቀበለ ፍርድ ቤትም ያለ አግባብ እያመላለሰ እውነተኛ ፍርድ መስጠት አለመቻሉን የታዘቡት የአካባቢው ነዋሪዎች፤ ጉቦ እንዲሰጡ እያደረጉት ያሉት ተንኮል ነው ሲሉ መናገራቸውን የተገኘው መረጃ ጨምሮ አሰረድቷል፣