Wednesday, October 29, 2014

በተለያዩ የሃገራችን ክልሎች ለሚኖሩ የትግራይ ክልል ተወላጅ ለሆኑት የመንግስት ሰራተኞች የትግራይ ክልል አስተዳደር ወደ ክልላችሁ ተመለሱ ብሎ ከስራቸው አፈናቅሎ ሲያበቃ የስራ ዕድል ስለከለከላቸው በከባድ የማህበራዊ ችግር ወስጥ ወድቀው እንደሚገኙ ምንጮቻችን አስታወቁ፣




እንደ-ምንጮቻችን መረጃ መሰረት በሃገራችን በሚገኙ ክልሎች በመንግስታዊ ስራ ተሰማርተው ለነበሩ የትግራይ ተወላጆች፤ በክልላችሁ ስራ ልንፈጥርላችሁ ነው በሚል ከሃቅ የራቀ የህወሃት ኢህአዴግን  ቅስቀሳ በማመን፤ ወደ ክልላቸው የተመለሱ ዜጎች የተገባላቸው ቃል በተግባር ባለመዋሉና ስራ በማጣታቸው ምክንያት ለከባድ የማህበራዊ ችግር ተጋልጠው እንደሚገኙ ሊታወቅ ተችሏል፣
    እነዚህ የችግሩ ሰለባ የሆኑ ዜጎቻችን “በተገባልን ቃል መሰረት የስራ እድል ይፈጠርልን፣” ብለው አቤቱታቸውን ባቀረቡበት ሰዓት፤ የትግራይ ክልል የማንነት መታወቂያ ስለሌላችሁ በክልላችን የስራ እድል አታገኙም እንደተባሉና ወደ ሚመለከተው አካል ደግመው አቤቱታቸውን ቢያቀርቡም፤ የሚሰማቸው ኣካል ማግኘት እንዳልቻሉ ምንጮቻችን አክለው አስታውቀዋል፣