Wednesday, October 29, 2014

በተለያዩ ምክንያቶች ጡረታ ወጥተው በማህበር የተደራጁና በተምቤን ከተማ ሲሰሩ የቆዩ ነባር የህወሃት ታጋዮችን ተቃዋሚዎች ናችሁ በማለት የገዥው ስርዓት ተላላኪዎች ከስራቸው እያፈናቀሏቸው መሆኑ ታወቀ፣





   ከአካባቢው በደረሰን መረጃ መሰረት እነዚህ ቀደም ሲል በትግል የቆዩና በጡረታ ተሸኝተው በተምቤን አብይ ዓዲ ከተማ በማህበር ተደራጅተው ኑሮአቸውን ሲመሩ የቆዩ ዜጎች፤ ራሳቸው ተደራጅተው ሲሰሩ ከቆዩበት ስራ፤ ያለምንም ምክንያት 5 ነባር ታጋዮች በወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ባለስልጣናት ሴራ እንደተባረሩ ተገለፀ፣
  እኚህ ወገኖች “እኛ ንፁሃን ዜጎች እያለን ለምን ከስራችን ተባረርን።” በማለት ዮናስ ወደ ተባለ የወረዳው አስተዳዳሪ በጠየቁበት ጊዜ ተገቢ ምላሽ ስላልሰጣቸው እንዳማራጭ በኮብልስቶን ስራ እንዲሰማሩ ያቀረቡት አቤቱታም ሰሚ ጆሮ እንዳላገኘ ሊታወቅ ተችሏል፣