Thursday, October 2, 2014

በሁሉም የትግራይ ክልል ዞኖች የሚገኙ ርእሰ መምህራን ከመስከረም 4 /2007 ዓ/ም ጀምረው በ2007 ዓ/ም ምርጫ ላይ አጀንዳ ያደርገ ቅስቀሳ በከፍተኛ ባለ-ስልጣኖች የተመራ በአክሱም ከተማ ተሰብስበው እንደሚገኙ ምንጮቻችን ከከተማዋ ገለፁ።



በመረጃው መሰረት በአክሱም ከተማ እየተካሄደ ያለው ስብሰባ የሰሜን ምእራብ፤ የማእከላዊና የምእራብ ዞኖች ርእሰ መምህራንና  ሌሎች ሙሁራን የተሳተፉበት ሁኖ ስብሰባው የመራውም አቶ ሓዱሽ ዘነበ የተባለ ከክልል የተላከ በለስልጣን እንደሆነና አላማውም መምህራን ከተማሪዎች ጋር ያላቸውን ቀረቤታ ተጠቅመው በዚህ አመት በሚካሄደው ምርጫ ላይ እድያሚያቸው ከ18 አመት በታች የሆንትም ጭምር በመመዝገ ለህወሓት እንዲመርጡ እንዲያባብሏቸው በማለት እንደሆነ ታወቀ።
   በዚህ መንገድ ርእሰ መምህራኑ በምርጫው ግዜ ተማሪዎች ተቃውሞ እንዳያስነሱ ክትትል ማድረግ እንደሚገባቸውና ከድርጅቱ ጎን ተሰልፈው የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡና አገራችን ውስጥ ባሉ የመልካም አስተዳደር ጉድለቶች ተንትርሰው ጥያቄዎች እንዳያስነሱና እንዳይቃወሙ ስጋት ላይ ስለወደቁ ለሚያጋጥመው ተቃውሞ እንዴት ማክሸፍ እንደሚችሉ ያለመ ደባ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።