በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ፀለምቲ ከተማ በሚገኘው ፖሊስ ፅሀፈት ቤት ተመድበው
በመስራት ላይ ያሉ የፖሊስ አዛዦች ህዝቡን ማገልገልና የህግ የበላይነት ከማረጋገጥ ይልቅ በፖለቲካ አይን ለሚጠረጥርዋቸው ሰዎች
በልዋሉበት ወንጀል እየያዙ እስከ ሞት ያሚያደርስ ከባድ ጉዳት እያደረሱባቸው መሆናቸውን ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።
ተጨማሪ የማአርግ
እድገት ለማግኘት ሲሉ የንፁሃን ዜጎች ሂወትን እየቀጠፉ ካሉ አዛዦች ውስጥ የማይ ፀብሪ ከተማ ፖሊስ ሃላፊ ምክትል ኮማንደር ፍስሃ ገብረመስቀል የተባለው ሲሆን ይህ ግለሰብ የአከባቢው
አስተዳዳሪዎች በፖለቲካ አይን በመጠርጠር ሲያይዋቸው የቆዩትን ሁለት ሰዎች መስከረም 2 / 2007 ዓ/ም ሰርቀዋል ብለው በመክሰስ
ህግ በማይፈቅደው መንገድ በዱላ ቀጥቅጠው ጉዳት ስላደረሱባቸው ሓጎስ አለበል የተባለው ወድያውኑ ህይወቱ እንዳለፈች ለማወቅ ተችሏል።
ይሁን እንጂ
የፈፀሙት ወንጀል ሳይኖራቸው ኢ-ሰብአዊ በሆነ መንገድ ሰዎችን እየገረፈ በመግደል ላይ ያለ የፖሊስ አዛዥ እስካሁን በላዩ ላይ የተወሰደ
እርምጃ ባለመኖሩ ምክንያት የከተማዋን ህዝብ ንጹኀን ልጆቻችን በማሰቃየት እየገደለ ያለው ፖሊስ ህግ ፊት ቀርቦ ሊጠየቅ ይገባል
እያሉ እንደሚገኙ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።