Wednesday, October 22, 2014

በትግራይ ምእራባዊ ዞን ሁመራ ከተማ የሚገኙ የህወሃት ኢህአዴግ ታጣቂዎች የግል ፍላጎታችሁን አናሟላም ላሉ ንፁሃን ወገኖች በመደብደብ እያሰቃዩዋቸው እንደሚገኙ ተገለፀ፣





   ምንጮቻችን ባደረሱን መረጃው መሰረት በሁመራ ከተማ ፀረ ሽፍታ ተብለው በአካባቢው አስተዳደር የተደራጁ ታጠቂዎች፤ ከፖሊስ አባላት ጋር በመተባበር በመጠጥና ምግብ ቤቶች ላገኟቸው ንፁሃን ሰዎች ለምን አልጋበዛችሁንም በማለት እያስቸገሯቸው እንደሆኑና፤ ፈቃደኞች ሳይሆኑ ለቀሩትም፤ ጭካኔ በተሞላበት መንገድ በመደብደብ አካላዊና ሞራላዊ ጉዳት እያደረሱባቸው እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፣
    ይህ በእንዲህ እንዳለ ፀጥታ በማስከበር ስም በፀረ ህዝብ ተግባር ተሰማርተው ለከተማው ነዋሪ ህዝብ ሰላም እያሳጡ ካሉ የስርዓቱ ተላላኪዎች፥ ተስፋይ ሓድጉ የተባለው ታጣቂ፥ ዋና ሳጅን ብርሃነ ከተባለ የፖሊስ አባል ጋር በመሆን ገነት ምግብ ቤት በተባለው አካባቢ ሃይለማርያም ለተባለ ግለ ሰብ። ይዟት ከነበረው ሞተር ሳይክል አስቁመው መጠጥ እንዲጋብዛቸው ጠይቀውት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ምክንያት፤ ሁለቱም ታጣቂዎች በግለሰቡ ላይ ድብደባ በማካሄድ ከባድ ጉዳት ማድረሳቸውና፤ ይህንን ሁኔታ የተገነዘቡት የአካባቢው ነዋሪዎችም ምሬታቸውን በማሰማት ላይ እንደሚገኙ፤ ያገኘነው መረጃ አክሎ አስረድቷል፣