Wednesday, October 22, 2014

በላዕላይ አድያቦ ወረዳ ህብረት በተባለው ቀበሌ የሚገኙ ሚልሻዎች ከዴምህት ጋር ትተባበራላችሁ ተብለው በፖሊሶች እየተያዙ በመታሰር ላይ እንደሚገኙ ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ፣





በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን፤ ላዕላይ አድያቦ ወረዳ ህብረት በተባለው ቀበሌ አካባቢ የሚገኙ ምልሻ፤ ጠላት ስለመጣ ተነቃነቁ የሚለውን የህወሃት ኢህአዴግ ካድሬዎች ትእዛዝ ባለመቀበላቸው ብቻ የዴምህት ተባባሪዎች ናችሁ ተብለው፤ በወረዳው ፖሊሶች ዓዲ ዳዕሮ ከተማ ተወስደው መታሰራቸውን። የደረሰን መረጃ አስታወቀ፣
    መስከረም 21/ 2007 ዓ/ም የዴምህት ተባባሪዎች ናችሁ ተብለው ከታሰሩት ሚልሻዎች መካከል የተወሰኑትን ለመጥቀስ ፍሰሃ ካህሳይ፤ሰለሞን አምባየ፤ ክፍሎም ታረቀና ሌሎችም እንደሆኑ ምንጮቹ ከአካባቢው አስረድተዋል፣