Wednesday, October 29, 2014

በወያኔ ኢህአዴግ ስብሰባ የሚሳካ የሽግግር እድገት የለም!!


የሽግግር ለውጥ የሚመጣው ትኽክለኛ አላማና መስመር በማስቀመጥ፤ ህዝቡ ለራሱ ጥቅምና ለሀገሩ እድገት ብሎ ተሳታፊ የሚሆንበት ዴሞክራሲያዊ ሁኔታዎችን በመፍጠር እንጅ። የገዛ ወገንን ፀረ ህዝብ በሆነ መንገድ አፍኖና አምበርክኮ በመግዛት አይደለም፣

የለውጥ ዋነኛ መሰረቱ የህዝቡ ንቁ ተሳትፎ ነው፣ ፍላጎቴን ሊሟላልኝ ይችላል፤ መንገዱ የእድገትና የሰላም መንገድ ነው ብሎ ራሱን ያሳመነ ህዝብ ካለ። ያለ መጠራጠር ለውጥ በማምጣት ላይ ችግር አይፈጠርም፣ በአንፃሩ ከሆነ ግን ለውጥ ማምጣት ይቅርና የነበረው እየተዳከመ ወደ ባሰው መጥፎ ሁኔታ መመለሱ አይቀሬ ነው፣
     በዚህ እይታ የስርአቱን የሽግግር መድረክ ስናየው እላይ ለመግለፅ እንደሞከርነው። ባገራችን ውስጥ ያለው የህዝቡ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት የመከበር ሁኔታ ጭራሹን የለም ተብሎ የሚነገርበት ሁኔታ ለይ ስለሚገኝ። አብዛኛው በስርአቱ እዲተገበሩ ተብለው የተያዙት ፕሮጀክቶች ኣብዛኘወቹ ከኣፍ ያልላለፈ ሁኖ ስቀሩ የተቀሩት ደግሞ ከተቀመጠላቸው የግዜ ገደብ። ሶስት አራት እጥፍ ወደ ኋላ እየተጓተቱ ማየት የተለመደ ነው፣ 
     ይህ በአሰራር ጥራት፤ በመሳርያ አቅርቦት ማነስ፤ በአመራሮች ላይ ያለው የግዴለሽነት አስተሳሰብ፤ አጠቃላይ ሰራተኛው ነገ የኔን ጥቅም የሚያስከብሩ ድርጅቶች ናቸው በማለት የመጭውን ብሩህ ተስፋ በሚያሳይ መንገድ አምነው ስለማይሳተፉበት እድገቱ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፣ ይህ የሚሆንበት ምክንያትም ስልጣን ላይ ያለው ስርአት የህዝቡ አገልጋይ ተደርጎ ስለማይታመንበትና ሁሉም እንቅስቃሴው በግል ጥቅሙ ላይ የተመሰረተ ስለ ሆነ ነው፣
      ባለፈው ሳምንት በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ውስጥ የተካሄደውና ለከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ያቀፈ ስብሰባም ይህንን የሚያንፀባርቅ እንደሆነና የስብሰባው ይዘትም ያገራችን የሽግግር እድገት አሁን ካለበት ደረጃ መራመድ አልቻለም በሚል ላይ ያተኮረ እንደነበረና። የዚሁ ዋነኛው ምክንያት ተደርገው ከተገለፁት ነጥቦችም።-

  •  ሁሉም አርሶ አደር እንደ ድርጅቱ አባላት አቅማቸውን አሟጥጠው የቴክኖሎጂ ውጤቶች ተጠቃሚዎች ያለመሆናቸው፤
  •  አርሳደሩ ጥራት ያላቸውና ለገበያ መዋል የሚችሉ ምርት ማምረት ያለመቻሉ፤
  •  ማዳባርያ፤ ምርጥ ዘር፤ ኮምፖስና የመሳሰሉትን ያለመጠቀም፤
  • ዘሩን በመስመር  ያለመዝራትና በእምነት ያለመጠቀም፤
  • ለፋብሪካዎች የሚውል ምርት በበቂ መጠን ያለማዘጋጀት። በሌላ ብኩል ደግሞ ምርት ቢቀርብም ምርቱን የሚጠቀሙ ፋብሪካዎች ያለመኖር፤
  • ለጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ኢዱስትሪ ሊያሳድጉ የሚችሉ ትላልቅና መካከለኛ ፋብሪካዎች ያለመኖር፤
  •  በመልካም አስተዳደር ላይ ለውጥ አልመጣም ብቻ ሳይሆን። ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ እንደሆነና። ህዝቡም በዚያው መጠን ብሶቱን እየገለፀ መሆኑ፤
  • የሊዝ ፖሊሲ አሰራር ግልፅ ባልሆነ መንገድ እየተሰራበት በመሆኑና በቂ የኮንዶምንየም መኖርያ ቤቶች ባለመገንባታቸው ምክንያት። ህዝቡ ስሜት ውስጥ መግባቱ፤
  • ሰራተኛው ሰርቶ ከሚያገኘው 30% ፐርሰንት በላይ ለኪራይ ቤት ክፍያ እያዋለው ስለሆነ ህዝቡ የሊዝ አሰራርን እንዳይቀበለው ዋናው ምክንያት እንደሆነ፤
  •  መሬት ያለ አግባብ እንዲከፋፈል መደረጉ። በተለይ በከተማዎች አካባቢ የሚገኘውን መሬት ወደፊት ወደ ከተማ መግባቱ ስለ-ማይቀረው በማለት። ህጋዊ ባልሆነ መንገድ መሬቱን እንዲሸነሸን ማድረግ የሚሉና ሌሎች ተዛማጅ ነጥቦች። የሽግግር እድገቱን እያኮላሹት ካሉት ተብለው ተዘርዝረዋል፣
    እነዚህ ከላይ የተገለፁትን ንጥቦች። ከረጅም አመታት ጀምረው የስርአቱ ሽማምንቶች እየሰሩበት የቆዩት ፀረ ህዝብ ተግባር እንጅ አሁን የተከሰቱ ችግሮች አይደሉም፣ የወያኔ እህአዴግ ካድሬዎች ግን አሁን እንደ ችግር ወስደው እያነሱት ያሉትን የህዝብ እሮሮዎች በመደበቅ በጥሩ ሁኔታ እየተጓዙ እንደሆኑ ሁነው ህዝቡን እያደናገሩ ቆይተዋል፣
    ለማንኛውም በእንደዚህ አይነት መድረክ ተሁኖ የሚመጣ የሽግግር እድገት። አቶ አባይ ወልዱ እንዳለው! እንቅፋቱን ካስወገድን ህዝባችን ይጠቀማል እኛም ከህዝባቸን ጋር አብረን እንጠቀማለን ብሎ እንደተናገረው ሳይሆን። የሽግግሩ መድረክ ከወዲሁ ጀምሮ ለነሱና ለግብረአበሮቹ ብቻ የጠቀመ፤ ባለምርጥ ቪላ መኖርያ ቤትና ባለ ዘመናዊ መኪናዎች እንዲሆኑ ያደረገ ሳጥናኤላዊ መንገድ እንደሆነ ሲበዛ ግልፅ ነው፣
    ለምን ዓላማ ተብሎ ነው ታድያ ይህ ሁሉ መላቅጡን ያጣ ስብሰባና ጋጋታ እየተካሄደ ያለው ከተባለ ግን። መልሱ ለፖለቲካዊ ፍጆታ፤ በህዝቡ ፊት የአዞ እንባ እያነቡ ለማደናገር፤ እየተዘጋጁበት ላለው አስመሳይ ምርጫ ደጋፊ ለማሰባሰብና የስልጣን እድሜያቸውን ለማራዘም ብለው እንደሆነ ለማንም ግልፅ ነው፣
    ለማጠቃለል።-  ያገሪቱ እድገት ይሁን የህዝቡ ጥቅም የሚረጋገጠው። ተከታታይ ስብሰባዎች በማካሄድና ምርጥ ምርጥ የሆኑ ወርቃማ ቃላቶችን በመናገር ሳይሆን። ተግባር ላይ ሊገለፅ የሚችል እንቅስቃሴና የህዝቡን ጥቅም ሊያረጋግጥ የሚችል ትክክለኛ አላማ ሲኖር ብቻ መሆኑ መታወቅ ይገባል፣