Wednesday, October 22, 2014

በትግራይ ምእራባዊ ዞን፤ ቃፍታ ሁመራ ወረዳ፤ ማይ ካድራ ከተማ ውስጥ በስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ዜጎቻችን በስርአቱ ፖሊሶች ገንዘባችውን እየተነጠቁ መሆናቸውን ምንጮቻችን ከአካባቢው ገለፁ፣




    በመረጃው መሰረት መስከረም 30/2007 ዓ/ም በቀን ስራቸው ውለው ወደ ከተማ እየገቡ ለነበሩ በርካታ ሰራተኞች የከተማዋ ፖሊሶች መንገድ ላይ አድፍጠው በመጠበቅና መሳርያቸውን አቀባብለው ገንዘባቸውን ለመንጠቅ በሞኮሩበት ግዜ፤ አብዛኛዎቹ አምልጠው ሲሸሹ የቀሩትን ወንጀለኞች በሚል መሰረት የሌለው ምክንያት በመደርደር። እስር ቤት ውስጥ እንዳስገቧቸው ለማወቅ ተችሏል፣
    ባልዋሉበት የሃሰት ወንጀል ከታሰሩት መካከል አንዳንዶችን ለመጥቀስ።- ሃጎስ ተኸለማርያም፤ ጓንሸ ማናሰብ፤ ይደግ ታየና ሌሎችም እንደሆኑ የገለፀው መረጃው፤ የከተማው ነዋሪ ህዝብ ምንም አይነት ጥፋት የሌላቸውንና ሰርተው የሚኖሩ ንፁሃን ሰዎች ለምን ይታሰራሉ ብሎ በጠየቀበት ሰዓት፤ ከህግ ውጭ መሳርያ ይዘው አግኝተናቸዋል ብለው የሓሰት መልስ መመለሳቸውና፤ በዚሁ ፀረ ህዝብ ስራ ከተሰማሩት የፖሊስ አባላትም ዋና ሳጅን ዓወት ሓዱሽ የተባለ እንደሚገኝበት መረጃው አክሎ አስረድቷል፣