Wednesday, October 22, 2014

በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን፤ ማይ ፀብሪ ከተማ የሚገኙ የህወሃት ኢህአዴግ ካድሬዎች የአካባቢውን ተማሪዎች በመሰብሰብ የህወሃት ሊግ አባላት እንዲሆኑ እያስገደዷቸው መሆናቸው ተገለፀ፣
    የማይ ፀብሪ ከተማ አስተዳዳሪዎች መስከረም 23/2007 ዓ/ም ተማሪዎቹን ከትምህርት ገበታቸው በማስተጓጎል ፖለቲካዊ ትምህርት ላይ ጠምደዋቸው ባሉበት በአሁኑ ጊዜ፤ የሊጉ አባላት እንደሚሆኑ በህወሃት ለተሰጣቸው አደራ ተማሪዎቹ በግዴታ ነው ወይስ በፍላጎት ብለው በጠየቁበት ሰዓት እኛ የሊጉ አባላት ናችሁ እያልናችሁ ነው። ይህንን አንቀበልም ያለ መድረኩን ረግጦ መውጣት ይችላል በማለት አስፈራርተው እንደመለሷቸው ለማወቅ ተችሏል፣
    በህወሃት ኢህአዴግ ካድሬዎች እኩይ ተግባር የተቆጡ ተማሪዎች የማስፈራርያውን መልስ ግምት ባለመስጠት  ስብሰባውን ለምን ጥላችሁ ሄዳችሁ ብላችሁ እንዳትጠይቁንና እንዳታስሩን በማለት መለይ ሓዱሽ፤ ታፈሰ አይናለምና ሌሎች ተማሪዎች መድረኩን ረግጠው በመውጣታቸው ብቻ፤ አደናቃፊዎችና ፀረ ልማት ናቸው። እንደነዚህ አይነቶችን ሳንመነጥር የሚሰራ ስራ የለም። አሁንም የቀራችሁ ካላችሁ መውጣት ትችላላችሁ በማለት። አስገድደው የህወሃት ሊግ አባላት እንዲሆኑ በማድረግ ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ መረጃው አክሎ አስረድቷል፣