Wednesday, October 29, 2014

በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን አስገደ ፅምብላ ወረዳ የሚገኙ የህወሃት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ሹማምንቶች ለመሰረተ ልማት ግንባታ ተብሎ ከህዝብ የተሰበሰበውን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት እንደሆኑ ምንጮቻችን ከስፍራው ገለፁ፣





  በአስገደ ፅምብላ ወረዳ የሚገኙ በሙስና የተጨማለቁ ካድሬዎች ለመንገድ መስሪያ ተብሎ ከህዝብ የተሰበሰበውን ገንዘብ  እንዳጠፋፉት የገለፀው መረጃው፤ በማጠፋፋቱ ተግባር ላይ ዋናው ድርሻ ከነበራቸው ባለስልጣናት መካከል፤ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሃሴት እንዲሁም የሚዛን ቀበሌ ዋና አሰተዳድሪ አቶ ሙሉዓለም አስገዶምና ሌሎችም እንደሚገኙበት መረጃው አስረድቷል፣
   በመጨረሻም እነዚህ የሃገርንና የህዝብን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው ያዋሉ የወረዳው አስተዳዳሪዎች ለጊዜው የታሰሩ ቢሆንም፤ ለማስመሰል ያደረጉት እንጂ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ያለምንም ምርመራና ህጋዊ ውሳኔ ይፈቷቸዋል በማለት፤ ነዋሪው ህዝብ በስርዓቱ ላይ እምነት እንደሌለው በመግለፅ ላይ እንዳለ መረጃው አክሎ አስረድቷል፣