Monday, October 27, 2014

በአዲስ አበባ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ትምህርታቸውን በግዴታ አቋርጠው በስርዓቱ ካድሬዎች ምርጫን በሚመለከት ቅስቀሳ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ምንጮቻችን ከከተማዋ የላኩልን መረጃ ገለፀ፣




እነዚህ ተማሪዎች መስከረም 25/2007 ዓ,ም ጀምረው በኢህአዴግ ካድሬዎች አስገዳጅነት ስብሰባ ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ የገለፀው ይህ መረጃ። የስብሰባው አጀንዳ ደግሞ ግንቦት 2007/ዓ,ም ለሚካሄደው ምርጫ የሚመለከት ሲሆን። ስብሰባው ሊጠናቀቅ ሁለት ቀናት ሲቀረው እነዚህ ተማሪዎች ስብሰባውን አቋርጠውት እንደወጡ የደረሰን መረጃ አመለከተ፣
    መረጃው አክሎ።- በአጠቃላይ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ጥላቻ በከፍተኛ ሁኔታ እያሰሙ መሆናቸውን በመግለፅ። በተለይ  በአሜሪካ የሚገኙ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን የኢትዮጵያ አምባሳደር በሚገኝበት ፊት ለፊት ያካሄዱት ስርዓቱን የማውገዝ ጠንካራ የሰላማዊ ሰልፍ ተቃውሞ። ከስርዓቱ ተላላኪዎች በስተቀር መላው የአዲስ አበባ ህብረተሰብም ሆነ  የሃገራችን ህዝብ  ልናደርገው  የሚገባን ተቃውሞ ነበር በማለት መነጋገሪያ አጀንዳቸው አድርገውት እንደሚገኙ የተገኘው መረጃ  አስረድቷል፣