Monday, October 27, 2014

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ። የመንግስት ሰራተኞችን በማስገደድ እየተካሄደ ባለው ስብሰባ ላይ። ለገዢው የወያኔ ኢህአዴግ መንግስት በርከት ያሉ ተቃውሞዎች እየቀረቡለት መሆኑን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አመለከተ፣




በመረጃው መሰረት። በአዲስ አበባ  አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ውስጥ ለሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች። ከጥቅምት 3 /2007 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ 11 ቀናት የቆየውን ስብሰባ በ9 ምድብ ተከፋፍሎ። በከፍተኛ የቴክኒክና ሞያ ማሰልጠኛ ኮለጅና። ሰፈረ-ሰላም ተብሎ በሚጠራው ት/ቤት አዳራሽ እየተካሄደ ባለው የግዴታ ስብሰባ ላይ። በርከት ያሉ ተሰብሳቢዎች ከፍተኛ ተቃውሞ በማሰማት ላይ እንደሚገኙ ተገለፀ፣
    በተሰብሳቢዎች ከቀረቡት ጥያቄዎች ገሚሶቹን ለመግለፅ።-
-          ኢህአዴግ በሃገር ውስጥ ሆነው ለሚታገሉ ተቃዋሚዎች የተመቻቸ ሁኔታ ስለማይፈቅድ። ካገር እንዲወጡና የትጥቅ ትግል ወደሚያካሂዱ ሃይሎች እንዲሄዱ እየተገደዱ ነውና ከዚህ ተሳስሮ መጪው ምርጫ ምን አይነት መልክ ይይዛል?
-          ገዢው የኢህአዴግ ስርአት ስለ ራሱ ጠንካራ ጎን እንጅ ደካማ ጎኑን አስመልክቶ ለህዝብ አይገልፅም፤ ይህንን ለሚገልፁ ተቃዋሚወችም እየታሰሩ ነው?
-          ኢህአዴግ አገራችንን ወደ ጥፋት መንገድ እየመራት ነው፤ አማራ ከኦሮሞና ሌሎች ብሄረሰቦችም በተመሳሳይ እንዲጋጩ እያደረገ ነው፤
-          ኢህአዴግ ስልጣኑን በሰላማዊ ምርጫ ለተቃዋሚ የሚያስረክብ መሆኑን ምን ማረጋገጫ አለን? ከ 97 ዓ/ም ምርጫ ላይስ ምንድነው የምንማረው?
-          ተቃዋሚዎች ለለውጥ እንጅ ለጥፋት እንደማይሰሩ እየታወቀ። ባገሪቱ ውስጥ ማንኛውም አደጋ ሲፈፀም የተቃዋሚዎች እጅ እንዳለበት ተደርጎ ለምን ይገለፃል የሚሉና ለመሳሰሉት ጥያቄዎች ተገቢ መልስ ስላልተሰጠባቸው። ሰራተኞቹ መሰብሰባችን ትርጉም የለውም በማለት ከፍተኛ ተቃውሞ ማስነሳታቸውን የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድተዋል፣