Monday, October 27, 2014

በአዲስ አበባና በመቐለ ከተማ የሚኖር ህዝብ በቅርብ ጊዜ በኢህአዴግ መሪዎች የተከበረውን የባንዴራ ቀን እንደተቃወመ ተገለፀ፣




በምንጮቻችን መረጃ መሰረት። በአዲስ አበባና በመቐለ ከተማ የሚኖር ህብረተሰብ በኢህአዴግ አምባገነን መንግስት የባንዴራ ቀንን እንዲያከብር የተደረገለትን ጥሪ በመቃወሙ ምክንያት ። በፌደራል ፖሊስና በደህንነት አባላት ሳይወድ በግድ በመሳሪያ ታጅቦ ወደ ስታዲዮም እንዲሄድ ብታደርጉም። ምንም አይነት ትርጉም የለውም  ህብረተሰቡ  ችግር ተደራርቦበት መፍትሄ አጥቶ እያለ የባንዴራ ቀን ብላችሁ እየፈፀማችሁት ያለው እኩይ ተግባር ፍፁም ከስነ-ምግባር ውጭ ነው በማለት በግልፅ ተቃውሞውን እንደገለፀ ለማወቅ ተችሏል፣
  የባንዴራ ቀን እየተባለ ከመጠን በላይ የሃገርንና የህዝብን ገንዘብ ከማባከን ይልቅ። ለተቸገር ህዝብ ማገዙ አይበጅም ወይ? ስኳር በመደበቅ እንዲወደድ በማድረግ ህብረተሰቡ በመንግስት ላይ ተቃውሞ እንዲያስነሳ ታደርጋላችሁ በማለት የምታስሯቸው ነጋዴዎች አግባብነት የለውም ሲሉ በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ጥላቻ እየገለፁ እንደሚገኙ መረጃው ጨምሮ አስታውቋል፣