Wednesday, October 22, 2014

በትግራይ ማዕከላዊ ዞን የአክሱም ከተማ ነዋሪዎች ከውጭ ሃገር ለሚመጡ ዲያስፖራ ኢንቨስተሮች መቀበያ ገንዘብ እንዲያዋጡ በካድሬዎች እየተገደዱ እንዳሉ ምንጮቻችን አስታወቁ፣





    የአክሱም ከተማ ነዋሪዎች ከውጭ ሃገር ለሚመጡ ዲያስፖራ ኢንቨስተሮች መቀበያ የሚሆን ገንዘብ አዋጥተው እንዲያዝናኗቸው የከተማዋ አስተዳዳሪዎች መስከረም 24/2007 ዓ,ም ህብረተሰቡን በመሰብሰብ መመሪያ እንዳወረዱላቸው መረጃው የገለፀ ሲሆን፤ የከተማዋ ነዋሪዎች ግን ነገም ይሁን ዛሬ የምናዋጣው ገንዘብ የለንም ስንት ጊዜ ልታታልሉን ነው በማለት በከተማዋ አስተዳዳሪ የቀረበውን ሃሳብ እንደተቃወሙት ለማወቅ ተችሏል፣