Wednesday, October 22, 2014

በሁመራ ከተማ የሚገኙ የማዘጋጃ ቤት ሃላፊዎች መሬት ለድሃው ህብረተሰብ እየከለከሉ ቆይተው ከውጭ ሃገር ለመጡ ወዳጆቻቸውና ሃብታሞች እየሸጡላቸው እንደሚገኙ ምንጮቻችን ገለፁ፣





  ከከተማዋ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው አብዛኛዎቹ  የሁመራ ከተማ ነዋሪዎች በመሬት እጦት ምክንያት እየተቸገሩ ባሉበት በአሁኑ ሰዓት፤ የማዘጋጃ ቤት ሃላፊዎች መሬት አይሸጥም አይለወጥም የመንግስት ነው እያሉ ከድሃው ህብረተሰብ እየቀሙ የቆዩትን የከተማ መሬት፤ በቅርብ ጊዜ  ከውጭ ለመጡ ሃብታሞች እየሸጡላቸው እንደሚገኙ ሊታወቅ ተችሏል፣
   በህወሃት ኢህአዴግ ካድሬዎች ከተሸጡት መሬቶች ውስጥ በመናሃሪያው አካባቢ የሚገኝ ሰፊ መሬት እንደ አብነት በመጥቀስ፤ ይህ ሰፊ መሬት ከድሃው ህብረትሰብ ተቀምቶ የቆየ እንደሆነና በቅርብ ጊዜ ግን እስራኤል ለሚገኝ ሃብታም ተሽጦ ታረቀ ምስግና ለተባለ ተወካይ እንደተሰጠ ታውቋል፣
 በዚህ ተግባር የተቆጡ የሁመራ ከተማ ነዋሪዎች ደግሞ በመሬት እጦት ምክንያት የተቸገረ  ህብረተሰብ እያለ ለሃብታምና ጉቦ ለሰጧችሁ ለምን ታድላላችሁ? ለምን ቅንነት ባለው መንገድ የማታስተዳድሩን እያሉ ምሬታቸውን እያሰሙ እንደሚገኙ ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ አክሎ አስረድቷል፣