Wednesday, October 22, 2014

በሽረ ከተማ የሚገኘው ሆስፒታል ለህብረተሰቡ ተገቢውን አግልግሎት ሊሰጥ ባለመቻሉ ምክንያት የሰው ህይወት እየጠፋ እንደሚገኝ ምንጮቻችን አስታወቁ፣




  የሽረ እንዳስላሴ ከተማ ነዋሪ ህዝብ በህክምና አገልግሎት ተቸግሮ እንዳለ የገለፀው፤ ይህ መረጃ በተለይ በከተማዋ ያለው ሆስፒታል ስርዓት ባለው መንገድ ስለማይተዳደር ለመታከም ብለው ለሚሄዱ ህመምተኞች በአግባቡ የሚከታተላቸው አካል አጥተው ለሞት የሚዳረጉ ወገኖች በርከት ያሉ እንደሆኑና። በቅርብ ጊዜም አቶ ምሩፅ አበራ የተባለ ዜጋ ልጁ በከባድ ታሞበት ሊያሳክመው ወደ ሆስፒታሉ ይዞት በሄደበት ሰዓት በዚህ ተራ ያዝ ተራህ አልደረሰም እያሉ በክትትል ጉድለት ምክንያት ልጁ ለሞት እንደተዳረገበት ለማወቅ ተችሏል፣
  መረጃው አክሎ በሆስፒታሉ የሚገኙ አንዳንድ ቅንነት የሌላቸው ሃኪሞች የዜጎቻቸውን ህይወት ለማዳን ተነሳሽነታቸው  በጣም የደከመ ከመሆኑ የተነሳ። ለተገልጋዩ ማህበረሰብ ምክንያቶችን እየፈጠሩ እያንገላቱት እንዳሉና ኮምፒውተራቸው ላይ ጌም እየተጫወቱ እንደሚውሉ መረጃው ግልፆ።  በዚህ የተነሳም ህፃናትና እናቶች የሚገኙባቸው ቁጥራቸው እጅግ በርካታ ሰዎች በገንዘባቸው ህክምና የሚሰጣቸው ሰው አጥተው በሆስፒታሉ ግቢ ውስጥ ህይወታቸው  እየጠፋ እንዳሉና። ሞያዊ ስነ-መግባር ከማይሰማቸው ዶክተሮች መካከልም ዶ/ር ዮናስ የሚባለው እንደሚገኝባቸው ምንጮቻችን አክለው አስታውቀዋል፣