በትግራይ ክልል በሚገኘው መብራት ሃይል ጽ/ቤት የትራንስፎርመርና ሌሎች
እቃዎች ግዢ ሃላፊ የሆነው አቶ ክፍሎም ቀሺ የተባለው ግለሰብ ባለፈው 2006 ዓ/ም ዓመታዊ በጀት ከትግራይ ክልል መብራት ሃይል
ጽ/ቤት ለትርንስፎርመር ግዢ ተብሎ የተሰጠውን በርካታ ገንዘብ፤ የህንድ አቅራቢ ድርጅት ከሆነው ጋር በመስማማት ጥራት የሌለው ትራንስፎርመር በመግዛት፤ ቀሪውን
ገንዘብ ለግል ጥቅሙ እንዳዋለው መረጃው አስታውቋል፣
ሃላፊው የያዘውን ስልጣን ተጠቅሞ የመንግስትን ገንዘብ እንዳጠፋፋ በሰራተኞቹ
ተነቅቶበት ለሚመለከታቸው አካላት መረጃው ቢደርስም፤ ተገቢው ክትትል ስላልተደረገበት መስከረም 28/2007 ዓ/ም ከአገር ወጥቶ
መጥፋቱን የገለፀው መረጃው፤ እየሰራበት የቆየው ሃላፊነትም ምክትሉ ለነበረውና አቶ ካህሱ ለተባለው ግለሰብ መሰጠቱን፤ የደረሰን
መረጃ ጨምሮ አስረድቷል፣