Thursday, November 13, 2014

የወያኔ ኢህአደግ ካድሬዎች በሑመራ ከተማ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችን ሰብስበው ወደ ውትድርና እንዲሰለፉ ጥቅምት 24 /2007 ዓ/ም ቅስቀሳ እንዳደረጉላቸው ምንጮቻችን ከከተማዋ አስታወቁ፣



   በምንጮቻችን መረጃ መሰረት እነኝህ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በተጠቀሰው ቀን ማታ ከ12 እስከ ሦስት ሰአት ምሽት የህወሓት ካድሬዎች በዝግ አዳራሽ ሰብሰበው፤ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የትግራይ ብሄር ተወላጅ በከፍተኛ አመራር ካልሆነ በስተቀር በታችኛው የሰራዊት አባል ግን የትግራይ ብሄር ተወላጅ የሚባል ስለሌለ ለዚህ ደግሞ እናንተ ልትሸፍኑት ይገባቸኋል በማለት፤ የትምህርት ቤቱ ዳሬክተር ከሌሎች የስርአቱ ካድሬዎች ጋር በመሆን በከፍተኛ ሁኔታ ቅስቀሳ እንዳደረጉላቸው ለማወቅ ተችሏል፣
  በተመሳሳይም በሃገር ደረጃ 10ና 12 የጨረሱ ተማሪዎች ወደ ውትድርና እንዲገቡ የገዢው ስርአት ካድሬዎች በልዩ ቅስቀሳ ተጠምደው እንዳሉም መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣