የኢህአዴግ
ገዢው መንግስት ከመስከረም ወር ጀምሮ ምርጫን አስመልክቶ ቅስቀሳ እያካሄደ ሲሆን ተቃዋሚዎቹ ግን ስርአቱ በሚያካሂዳቸው የማደናቀፍ
ተግባር ሳቢያ እስካሁን ቅስቀሳ ለማድረግ እድል እንዳላገኙ የተገኘው መረጃ አስታውቋል፣
ባለፈው ሳምንት በተካሄደ የምርጫ ቦርድ ስብሰባ የምርጫ ቦርድ ሃላፊው
ባስተላለፈው መልእክት ላይ፤ ተቃዋሚዎች ካሁን ጀምረው ህዝቡን በመሰብሰብ ቅስቀሳ ማድረግ እንደሚችሉና፤ ከጥር 2007 ዓ/ም ጀምረውም
የመገናኛ ብዙኃን ሽፋን እንደሚሰጣቸው በሚድያ ቢገለፅም፤ ከአለም ማህበረሰብ ፊት ዴሞክራሲያዊ መስሎ ለመታየትና የኢትዮጵያን ህዝብ
ለማደናገር እንጂ፤ ሃቅነት እንደሌለው ህዝቡ በሰፊው እየተነጋገረበት
እንዳለ ታውቋል፣
ይህ በንዲህ እንዳለ ለአምስተኛ ግዜ ሊካሄድ ታስቦ ያለውን የ2007 ዓ.ም
አስመሳይ ምርጫ፤ የተቃዋሚ መሪዎችና አባላት ኢህአዴግን በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ከስልጣኑ እናስወግደዋለን የሚሉት ተቃዋሚ ድርጅቶች
ፕሮግራማቸውና እቅዳቸው ለህዝቡ ለማስተዋወቅ በሞከሩበት ግዜ፤ የስርአቱ የፀጥታ ሓይሎች የተለያዩ ሰንካላ ምክንያቶችን እየፈጠሩ
እያሰሯቸው እንደሆኑ መረጃው አክሎ አስረድቷል፣