Saturday, November 1, 2014

የፍዳ ቀጠሮ!! ሁለተኛ ክፍል!




የተከበራችሁ ውድ ተከታታዮቻን ባለፈው ሳምንት “የፍዳ ቀጠሮ” በሚል ርእስ ያቀረብነውን ሁለተኛ ክፍል ወደ ናንተው እናቀርበዋለን። መልካም ቆይታ
   እስከ 1997 ዓ/ም ሦስተኛው ብሄራዊ ምርጫ ድረስ። ብዙዎቹ ተስፋ ነበራቸው። ከፋፍሎ ገዢዎች በአፋቸው እየመረቁ በልባቸው እየረገሙ ይቀባጥሩት የነበረውን “ጅብ የበግ ለምድ ለብሶ ብጤ አካሄድ” እውነት ይመስላቸው ነበር፣ ያሉትን ቃል፤ የነገዱበትን የህዝብ ልጅና የሰማእታትን ደም ያላወቀው ብዙ ነበር፣
    “የሌባ አይን ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ” እንደሚባለው በ1997 የግንቦት ሰባት የፍዳ ቀጠሮ። መድብለ ፓርቲ ስርአት (Multy Party System) እንገነባለን በማለት በቀባጠሩት አፋቸው። ህዝብ ሙሉ በሙሉ ድምፁን በማሰማት አንፈልጋችሁም፤ በቃችሁን ቢላቸው ዘመን ያማይሽረውን ግፍ በጭዋው ህዝብ ላይ ፈፀሙ፣
     በዚህ ሦስተኛ “የመክራ ቀጠሮ” ስውር የነበረውን ደባ በሙሉ ግልፅ ሆነ፣ ባንድ ወገን የወያኔ ኢህአዴግ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ መስመርን የማይፈልገው መሆኑ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የወያኔዎች አፍ’ና ልብ የተለያየ መሆኑ በአደባባይ በጠራራ ፀሃይ ታየ፣
     ከዝያ በፊት ይጠቀሙበት የነበረውን በድብቅ የመግደል ተግባራቸውን። ባሁኑ ግዜ ይፋ ወጥቶ አፈሙዝ አምላኪዎችነን ብለው በጠራራ ፀሃይ በሃገሪቱ ዋና ከተማ በአዲስ አበባ ብቻ ከ200 በላይ ንፁሃን ዜጎወቻችን ከአግአዚና ፌደራል ፖሊስ በዘነበው የጥይት በረዶ። ህይወታቸውን ኢድያጡ ተደርገዋል፣ በሌሎች የሃገሪቱ ክፍለሃገር፤ ከተሞችና የገጠር አካባቢዎች የተገደሉት ሲጨመርበት በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወታቸውን ያጡ መሆኑን መገመት አያዳግትም፣
     ይህ ብዙዎች አካለ-ጎደሎ የሆኑበትና በወቅቱ ይፈፀም በነበረው ፈርኦናዊ ግፍ። ሰላምታ መለዋወጥን ጨምሮ ሰው ከሰው እንዳይገናኝ ያገደ፤ በወቅቱ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የቅንጅት ላንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (ቅንጅት) አመራሮች፤ አባላትና ደጋፊዎች ወደ ወህኒ ሲወረወሩ። ብዙዎችም በስውር ተገድለዋል፣ ለምሳሌ።- በብርሸለቆ ማጎሪያ ካምፕ ውስጥ ታጉሮው ከነበሩ የህሊና እስረኞች መካከል በሌሊት “ውጣ ለምርመራ ትፈለጋለህ ” እየተባሉ ተወስደው ደብዛቸው የጠፉና ዘመድ ቤተሰብ አልቅሶ ያልቀበራቸውን ንፁሃን ዜጎች። ታሪክ ለዝንተ አለም አይረሳውም፣ በካምፑ ውስጥ የነበረው እስረኛ - ”ለምን እየተጠሩ የሚወሰዱትን እስረኞች አይመለሱም ? የሚል ጥያቄ ሲያነሳ ወደ ሌላ ማረምያ ቤት ተዘዋውረዋል፣ “ ለምንስ ጥይት ይተኮሳል? ለሚለው ደግሞ “ ውሻና ጅብ ሌሊት ስለሚመጡብን እነሱን ለመግደል ነው” ተብሎ የተነገረበት ግዜም በዚህ ወቅት ነበር፣
     እናም! ዛሬ የቅንጅት ፓርቲ አመራሮች ግን የጨው ዘር ሆነው ቀርተዋል፣ ያ ታሪክ ደግሞ ላይደገም ሁሉም አማራጩን ያዘ፣ በከፋፍለህ ግዛው ማሌሊታዊ መርዝ ምክንያት አንድነት በወያኔ-ኢህአዴግ ዘመን የማይታይና የማይነሳ መስሎ ተቀበረ፣
    ከዚህም የተነሳ በአራተኛው “የፍዳ ቀጠሮ” በምርጫ 2002 ዓ/ም የህዝብን ቀልብ በማዛባት የሃገሪቱን የወደፊት መልካም እድል ማስተካከል የሚችል ፓርቲ እንዲጠፋ ከተደረገ በኋላ። በአንፃሩ 62 በላይ ተቃዋሚ ነን የሚሉ ፓርቲዎች ብቅ አሉ፣ ተቃውሟቸው የይስሙላ በመላ፤ ስራቸው የከፋፈለህ ግዛው ህልም ተርጓሚ እና ሰላይ ሆነው ህዝብን ማደናገር ነበር፣ ይህም ወንዝ አፍራሽ ሳይሆን ኢህአዴግ በራሱ አደራጅቶ መድብለ ፓርቲ ስርአት እያለ። ከአለም ማህበረሰብ የሚከለልበትና መስሎ ለመኖር ያደረገው ሴራ ነው፣
    ከእነዚህ መካከል አንድ ሁለት እውነተኛ ተቃዋሚ ድርጅቶች ቢኖሩም። አባሎቻቸው ሲገደሉ፤ ሲታሰሩ፤ ሲገረፉ፤ አካላቸው ሲጎድልና ንብረታቸው ሲዘረፍ ማየት። አዲስ ነገር አልነበረም፣