Monday, January 26, 2015

በሑመራ ከተማ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች ንግድ ፍቃድ አላደሳችሁም በሚል ምክንያት ለበርካታ ነጋዴዎች ከገቢያቸው በላይ እንደቀጧቸው ተገለጸ።



    እንደ ምንጮቻችን መረጃ መሰረት በሑመራ ከተማ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች ንግድ ፍቃድ አላደሳችሁም በሚል ምክንያት ለባለሃብቶችና ሸቀጣሸቀጦች ለሚነግዱ ዜጎች ከ 3ሺ እስከ 60ሺ ብር እንዲቀጡ መደረጉና ከተቀጡት ነጋዴዎች የተወሰኑትን ለመጥቀስ ግርማይ አባይ የተባለ ልጉዲ ሆቴል የተከራየ ነጋዴ 40ሺ ተቐጥቶ ሆቴሉ እንዲታሸግ፤ ጀማል ስዒድ የጫት ንግድ የነበረው 20ሺ ብር፤ ወ/ሮ መብርሂት ገብረመስቀል የተባለች ሆቴል ባለቤት 3ሺ ብርና ሌሎች ባለድርጅቶችም ከአቅማቸው በላይ ገንዘብ እንዲከፍሉ እንደተወሰነባቸው ታውቋል።
   ይህ በንዲህ እንዳለ ከነዚህ ነጋዴዎች ውስጥ ቤት ተከራይተው የሚነግዱ የነበሩ በመሆናቸው ምክንያት ይህን ያክል ገንዘብ አንከፍልም፤ ንግድ ፍቃዳችሁን ውሰዱ ብለው እንደጣሉላቸውና የገቢዎች ክፍል ሰራተኞች ግን እኛ አስከፍሉ ተባለን ነው እንጂ ስለውሳኔው የምናውቀው ነገር የለንም ብለው ቢናገሯቸውም የሑመራ ከተማ ነዋሪ ህዝብ በአስተዳደሩ የተዛባ አስራር ምሬቱን በመግለፅ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።