Monday, January 26, 2015

በትግራይ ክልል ምእራባዊ ዞንና አካባቢው ተከስቶ ባለው ግጭት የስልክ አገልግሎት በመቛረጡ ምክንያት ነዋሪው ህዝብ እለታዊ ኑሮውን እንዳያሳልጥ እንቅፋት ሁኖበት እንደሚገኝ ተገለፀ።



    ምንጮቻችን እንደገለፁት በአካባቢው ተከስቶ ባለው ግጭት በግዜው መፍትሄ ባለማግኘቱ የተነሳ የአማራና የትግራይ ክልል አስተዳዳሪዎች ተከስቶ ያለው ጉዳት በብዙሃን መገናኛ እንዳይሰራጭ ሲሉ ከምእራባዊ ዞን እስከ ታሕታይ አድያቦ የስልክ አገልግሎቱን በመዝጋታቸው ምክንያት የአካባቢው ነዋሪ ህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊው ስራውን እንዳያከናውን እጅግ ተቸግሮ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
    ከዞኑ ሳንወጣ በሑመራ ከተማ የሚኖር ህዝብ የምርጫ ምዝገባ ተጀምረዋል ተብሎ ራሱ ካርድ ስላልወሰደ አስተዳዳሪዎች ለነዋሪው ህዝብ በሃይል አስገድደው ሊያስወጡት ሞክሮው አንወጣም ስላላቸው በአስተዳዳሪዎችና በህዝቡ መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ  እንደሚገኝ የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።