Thursday, January 22, 2015

በወልቃይት ለሚገኘው የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክት መስሪያ ተብሎ የሚላከውን የህንፃ ማከናወኛ ቁሳቁስ የፕሮጀክቱ ሓላፊዎች እየሸጡ ለግል ሃብታቸው እያዋሉት መሆናቸውን ምንጮቻችን አስታወቁ።



   መረጃው እንደገለፀው በትግራይ ክልል ምዕራዊ ዞን እየተሰራ ነው ለሚባልለት የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክት መሳሪያ እየተባለ ለሚላከው የህንፃ ቁሳቁስ የፕሮጀክቱ ሃላፊዎች ከግል ነጋዴዎች ጋር እየተመሳጠሩ በመሸጥ ለግል ሃብታቸው እያደረጉት መሆናቸውን ከገለፁ በኋላ በተለይ የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ዶክተር ገብረመስቀል የተባለ ግለሰብ ከንብረት ክፍሉ ጋር በመሆን እንደ ተንዲኖ፤ ሲሚንቶ፤ ቆርቆሮና ሌሎችንም ንብረቶች በመኪና በመጫን ወደ ጎንደር ከተማ ወስዶ  እንደሸጠው ለማወቅ ተችሏል።
   እነዚህ የሃገርንና የህዝብን ንብረት እየሰርቁ በመሸጥ ላይ ያሉት ሃላፊዎች የሰረቁትን የህንፃ መሳርያ ታህሳስ 25/ 2007 ዓ.ም በታርጋ ቁጥር  21652ና 16523 በሚታወቁ ሁለት መኪናዎች ጭነው በጎንደር ከተማ ለሚገኝ አቶ ተመስገን ‘ለተባለ የመጋዝን ባለቤት እንደሸጡለት ሊታወቅ ተችሏል።