Wednesday, January 28, 2015

የመከላከያ ሰራዊትና የፖሊስ አባላት ለገዥው ቡድን ኢህአዴግ ተገዥ በመሆን የሲቪል ልብስ በመልበስ የምርጫ ካርድ በመዉሰድ ላይ እንደሚገኙ ምንጮቻችን አስታወቁ።




ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ እንደሚያመለክተው በመቐለና በአዲግራት ከተማ አካባቢ ሰፍረው የሚገኙ የወታደርና የፖሊስ አባላት በአካባቢው ህብረተሰብ እንዳይታወቁ በመስጋት የሲቪል ልብስ ለብሰው ጥር 7/2007.ዓ.ም ወደ ምርጫ ጣብያዎች በመሄድ የምርጫ ካርድ እንደወሰዱ ለማወቅ ተችሏል።
    በስርዓቱ ህገ መንግስት ወታደር ይሁን የፖሊስ አባል ከማነኛውም የፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነ ነፃ ሁኖ በሃገሪቱ ለሚንቀሳቀሱና ለሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እኩል በማየት ያለምንም ወገንተኝነት ፀጥታ ማስከበር እንዳለበት የሚገለፅ ቢሆንም የስርዓቱ ቡድን አመራሮች ግን ይህንኑ ህግ በመጣስ ወታደሮችና የፖሊስ አባሎች  የኢህአዴግን ቡድን አጋር ሁነው እንዲመርጡ እየተደረገ መሆኑን መረጃው አክሎ አስታውቋል።