ደርባን ትራንስፖርት ከአዲስ አበባ ወደ አባይ ግድብ ስሚንቶና ሌሎች እቃዎች ሲያመላልስ የቆየ መሆኑን የጠቆመው
መረጃው። በአሁኑ ግዜ ግን መንግስት ተገቢውን የነዳጅ አቅርቦት ባለ ማድረጉ ምክንያት ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም። አወንታዊ ምላሽ
ባለ ማግኘታቸውና። እለታዊ ስራቸውን ለመስራት በመቸገራቸው ምክንያት። ሰራተኞቹ ተቃዉሞ ለማድረግ እንደተገደዱ ለመረዳት ተችለዋል፣
መረጃው ጨምሮ
እንዳስረዳው የድርጅቱ ሰራተኞች ከጥር 13 እስከ 15/
2006 ዓ/ም ስራ በማቆም ተቃዉማቸዉን በመቀጠላቸው ምክንያት። የግድቡ ስራ ሊስተጓጎል እንደቻለ። ከአከባቢው የደረሰን መረጃ አክሎ
አስረድተዋል፣
የህወሓት ኢህአዴግ ባለስልጣናት የአባይ ግድብ ግንባታ ከሁሉም በፊት ትልቅ
ቦታ የሚሰጠው ነው የሚሉ ቢሆኑም። በተግባር ላይ ሲታይ ግን ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ለስራው በሚያደናቅፍ ተግባር ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ
ይታወቃል፣