Wednesday, February 25, 2015

በዓዲ ነብሪኢድ የሚገኙ የህወሃት የፀጥታ አባላት ጥር 30/2007 ዓ.ም ከተማዋን በመክበብ ህብረተሰቡን እያስፈራሩ በመፈተሽ ስራ ላይ ተሰማርተው እንደዋሉ ታወቀ።



    በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ላዕላይ አድያቦ የሚገኙ የህወሃት ኢህአዴግ ካድሬዎች በተቃዋሚ ድርጅቶች እንቅስቃሴ ፍርሃት ውስጥ ወድቀው እንደሚገኙ የገለፀው ይህ መረጃ በተጠቀሰው ዕለት ፖሊሶችና ሌሎች ታጣቂዎችን በማሰማራት የዓዲ ነብሪኢድ ከተማ ነዋሪ ህዝብ ንብረቱን እየፈተሹና ከየት መጣህ እያሉ ሲያስፈራሩት እንደዋሉ ለማወቅ ተችሏል።
   በካድሬዎች ተግባር ትግስቱ የተሟጠጠው ህዝብ  ምን ስላደረግን ነው በአውላላ ሜዳ ላይ የግል ንብረታችንን የምትፈትሹት? የሚያስፈራችሁ ነገር ካለ በእንደዚህ አይነት መንገድ የሚድን ስርዓት የለም? ህዝብን ማንገላታትና ማስፈራራት አሁን ላለው ስርዓት የሚከላከልለት አይነት መንገድ አይደለም በዚህ አይነት መንገድ የሚያመልጥ ስርዓት ቢኖር ኑሮ ደርግ ከሽንፈት በዳነ ነበር በማለት የአካባቢው ነዋሪዎች መነጋገርያ አጀንዳቸው አድርገውት እንደሚገኙ መረጃው አክሎ አስረድቷል።