Sunday, March 1, 2015

በምስራቅ ጎጃም ዞን፤ በደብረማርቆስ ከተማ ዙሪያ የጎዛምን ወረዳ የብአዴን ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ አባላት ባደረጉት ስብሰባ ላይ አለመግባባት መፈጠሩን ከውስጥ የደረሰን መረጃ አመለከተ።



የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው የጎዛምን ወረዳ የብአዴን ኢህ.አ.ዴ.ግ አባላት  በደብረማርቆስ ከተማ ቀበሌ 03 በሚገኘው የወረዳው አዳራሽ ጥር 23 እና ጥር 24 2007 ዓ/ም በጎዛምን ወረዳ የብአዴን ጽህፈት ቤት ሃላፊ በመሃሪ አያል መድረክ መሪነት የቀጣዩን ምርጫ እንዴት ማሸነፍ አለብን፤ በወረዳችን በተደጋጋሚ የሚታዩ የተማሪዎችን ሰላማዊ ሰልፎችና  እንቅስቃሴዎች እንዴት መግታት አለብን በሚል የቀረበውን አጀንዳ እንዳልተቀበሉት የገለፀው መረጃው የተቃዋሚ የድርጅት አባሎቹ በተለያዩ አጋጣሚዎች እየታሰሩ የሚገኙት ተማሪዎች ወንድሞቻችን ናቸው ስለዚህ ጭካኔ የተሞላበት ስራ ከመስራት መቆጠብ ማቻል አለብን በማለታቸው የተናደደው መሃሪ አያል። በበርካታዎቹ የብአዴን-ኢህአዴግ ኣባልቱ ላይ ከፍተኛ ዛቻና ማስፈራራት የተሞላበት ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ተገለፀ።
     በተጨማሪም  መረጃው እንደጠቆመው በስብሰባ የሰነበቱት የድርጂት አባሎች በተከፈላቸው ዝቅተኛ የውሎ አበል ምክንያት እንደተበሳጩም መረጃው አክሎ አስርድቷል።