እንደምንጮቻችን
መረጃ መሰረት ገዥው መንግስት መጪውን ምርጫ አስመልክቶ ስጋት ላይ በመውደቁ ምክንያት ከዚህ በፊት ታማኝ ሆነው ሲሰሩ የቆዩ በርካታ
አመራሮችን ከስራ ገበታቸው እያገደ መሆኑና ከታገዱት መካከልም በምዕራብ ጎጃም ዞን፤ ቡሬ ወረዳ፤ የቁጭ ከተማ ዋና አስተዳዳሪ የነበረው አቶ አንዷለም አይሸሽምን ጥር 16 ቀን 2007
ዓም ሙስና በልቷል በሚል ባልዋለበት ስራ መትገዱና በአዊ ዞን ጃዊ ወረዳ የባምብሉክ ከተማ አስተዳዳሪ የነበረው እና ሌሎችም መሆናቸውን
ለማወቅ ተችሏል።
በተጨማሪም በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉትን የመኢአድ አባላት የነበሩ ንፁሃን
ዜጎችን እያፈሱ በማሰር ተግባር መጠመዳቸውን በመግለፅ ከአዊ ዞን ዚገም ወረዳ 4 የመኢአድ አባሎችና በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ወረዳ
2 ወጣቶችን የአሸባሪዎች ተላላኪና የምርጫ አደናቃፊዎች ናቸው በሚል
የሃሰት ውንጀላ በላያቸው ላይ ከፍተኛ ድብደባ በመፈጸም እንዲታሰሩ መደረጉን መረጃው አክሎ አስረድቷል።