Sunday, March 1, 2015

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ ከማሽ ዞን፤ በአንዳንድ ወረዳዎች በተደረገ የሰንደቅ አላማ መቀየር ምክንያት በርካታ ዜጎች እንደታሰሩ ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን አስረድተዋል።



 በክልሉ ከማሽ ዞን የሚገኙ  ነዋሪዎች  ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በክልላችን የሚደረገው የሌሎች ክልሎች ጣልቃ-ገብነት ይቁም፤  ህዝባችን የመረጠው እንጂ ሌሎች ክልሎች የመረጡት መሪ አያስተዳድረንም በማለት አቤቱታና ሰላማዊ ሰልፍ ያቀረቡ ቢሆንም ምንም ሰሚ አካል ባለማግኘታቸው የተነሳ ባለፈው ሳምንት ሰማያዊ፤ ነጭና ጥቁር መካከሉ ደግሞ ቀይ የV ቅርፅ ያለው ሰንደቅ አላማ  ማውለብለባቸውን የገለፀው መረጃው  የክልሉ ተወላጅ የሆኑ የቀድሞ ባለስልጣናት የነበሩ በርካታ ዜጎች በመንግስት ፖሊሶች የታሰሩ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል። 
    ይህ በእንዲህ እንዳለ በክልሉ የተሰማሩ ባለሃብቶች ባጋጠመው ግርግር ምክንያት እለታዊ ስራችንን መስራት አልቻልንም፤ በዚህ ከቀጠለም ለደህንነታችን አስጊ ነውና ባለፈው የምርት ዘመንም ለኪሳራ ተጋልጠናል ሲሉ ከስፍራው እየለቀቁ መሆናቸውን ምንጮቻችን አክለው ገልፀዋል።