Wednesday, March 25, 2015

በኦሮሚያ ክልል የአረጃ ወረዳ ነዋሪ የሆነው ህዝባችን ችግሮቹን በሰላማዊ ሰልፎች እንዳይገልፅ ስለተከለከለ አድማ ሊያነሳ ነው በማለት የስርዓቱ ካድሬዎች በስጋት ላይ ወድቀው እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አመለከተ፣



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት።- መጋቢት 3/2007 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል አርጃ ወረዳ የሚኖረው ህዝባችን እያጋጠሙን ላሉት ችግሮች በሰላማዊ ሰልፍ መልክ ተቃውሞአችንን መግለፅ አለብን በማለት ላቀረቡት ጥያቄ። በስርዓቱ የወረዳ አስተዳዳሪዎችና ካድሬዎች አንፈቅድም የሚል መልስ የተሰጣቸው ሲሆን። ህዝቡ በበኩሉ የአፈሙዝ ትጥቃችሁን በመተማመን አንፈቅድም ብትሉንም እኛ ግን ሰላማዊ ሰልፍ ከማድረግና ከመቃወም ወደ ኋላ አንልም የሚል ድምፅ እያሰማ እንደሚገኝ ሊታወቅ ተችሏል፣
በዚህም ምክንያት በከባድ ስጋት ላይ  የወደቁት የስርዓቱ ካድሬዎች ዛሬ  ነገ አድማ ይነሳል ከሚል ጭንቀት የተነሳ በከተማዋ በርካታ የፀጥታ አካላት አሰማርተው  ሃይለኛ ጥበቃ እያካሄዱ እንደሚገኙ ምንጮቻችን አክለው አስታውቀዋል፣